إعدادات العرض
ሶላትን የረሳ ሰው ባስታወሰው ጊዜ ይስገድ። ከዚህ በቀር ማካካሻ የለውም።
ሶላትን የረሳ ሰው ባስታወሰው ጊዜ ይስገድ። ከዚህ በቀር ማካካሻ የለውም።
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ሶላትን የረሳ ሰው ባስታወሰው ጊዜ ይስገድ። ከዚህ በቀር ማካካሻ የለውም። {ሶላትንም (በርሷ) እኔን ለማስታወስ ስገድ።} [ጣሀ:14]
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa తెలుగు Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली മലയാളം Bosanski ಕನ್ನಡ Kurdî Oromoo Română Shqip Soomaali Српски Wolof Українська Tagalog தமிழ் Moore Azərbaycan فارسی ქართული 中文 Magyar Português Deutsch Македонски Русский bmالشرح
የትኛውንም የግዴታ ሶላት ወቅቱ እስኪወጣ ድረስ መስገድን የረሳ ሰው ባስታወሰ ወቅት ቀዷእ ለማድረግ መፍጠን እንደሚገባውና አንድ ሙስሊም በወቅቱ መስገድን በመተዉ ለፈፀመው ወንጀልም ባስታወሰ ወቅት መስገዱ እንጂ ሌላ ምንም ማበሻና ማስማሪያ እንደሌለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ። አላህ በተከበረው መጽሐፉ እንዲህ ብሏል {ሶላትንም (በርሷ) እኔን ለማስታወስ ስገድ።} [ጣሀ:14] ማለትም የተረሳን ሶላት ባስታወስካት ወቅት ቀጥ አድርገህ ስገድ ማለትም ነው።فوائد الحديث
የሶላት አንገብጋቢነት እና በወቅቱ ከመፈፀምና ቀዷእ ከማድረግ መሳነፍ እንደማይገባ መገለፁን እንረዳለን።
ያለሸሪዓዊ ምክንያት ሶላትን ከወቅቱ ሆን ብሎ ማዘግየት እንደማይፈቀድ እንረዳለን።
የረሳ ሰው ባስታወሰ ወቅት፣ የተኛ ሰው ደግሞ በነቃ ወቅት ሶላትን ቀዷእ ማድረግ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
በተከለከለ ወቅት እንኳን ቢሆን ሶላትን በፍጥነት ቀዷእ ማድረግ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።