አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ ይስገድ።

አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ ይስገድ።

ከአቡ ቀታዳ አስሰለሚይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ ይስገድ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

በማንኛውም ወቅትና ለማንኛውም አላማ መስጂድ የመጣና የገባ ሰው ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ እንዲሰግድ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አነሳሱ። ይሀውም ሁለቱ የተሒየተል መስጂድ ረከዓዎች ናቸው።

فوائد الحديث

ከመቀመጥ በፊት የተሒየተል መስጂድ ሁለት ረከዓ መስገድ እንደሚወደድ እንረዳለን።

ይህ ትእዛዝ መቀመጥ ለፈለገ ሰው ነው። መስጂድ ገብቶም ሳይቀመጥ የወጣን ሰው ትእዛዙ አይመለከተውም።

አንድ ሰጋጅ ሰዎች ሶላት ውስጥ ሆነው መስጂድ ቢገባና ቀጥታ እነርሱ ወደሚሰግዱት ሶላት ቢገባ ከሁለቱ የተሒየተል መስጂድ ረከዓ ያብቃቃዋል።

التصنيفات

የፈቃደኝነት ሶላቶች, የመስጊዶች ህግጋት