إعدادات العرض
"የአላህ ቃል የበላይ እንድትሆን አስቦ የተዋጋ ሰው በአላህ መንገድ ተጋደለ የሚባለው እርሱ ነው።" አሉ።
"የአላህ ቃል የበላይ እንድትሆን አስቦ የተዋጋ ሰው በአላህ መንገድ ተጋደለ የሚባለው እርሱ ነው።" አሉ።
ከአቡ ሙሳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለጀግንነት ስለሚጋደል፣ ለወገንተኝነት ስለሚጋደልና ለይዩልኝ ስለሚጋደል ሰው ተነስቶ ‹በአላህ መንገድ የተጋደለው የትኛው ነው?› ተብለው ተጠየቁ። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "የአላህ ቃል የበላይ እንድትሆን አስቦ የተዋጋ ሰው በአላህ መንገድ ተጋደለ የሚባለው እርሱ ነው።" አሉ።
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Français ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî മലയാളം Kiswahili සිංහල Русский دری Svenska অসমীয়া ไทย Tiếng Việt Кыргызча Yorùbá ગુજરાતી Malagasy नेपाली Oromoo Română Nederlands Soomaali پښتو తెలుగు Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Српски Wolof Moore Lietuvių ქართული Українська Čeština Magyar Македонски Azərbaycanالشرح
ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተዋጊዎች አላማ ስለመለያየት ተጠየቁ። ለጀግንነት ወይም ለወገንተኝነት ወይም ደረጃው ሰው ዘንድ እንዲታይለት ወይም ከዚህ ውጪ ላለ አላማም ከተጋደለ ሰው መካከል በአላህ መንገድ ተጋደለ የሚባለው ማንኛው ነው? ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአላህ መንገድ የሚጋደል የሚባለው ሰው የአላህ ቃል የበላይ እንድትሆን የተጋደለ ሰው መሆኑን ተናገሩ።فوائد الحديث
የሥራዎች መስተካከያና መበላሻው መሰረቱ ኒያና ሥራን ለአላህ ማጥራት ነው።
የጂሃዱ መሰረታዊ አላማ የአላህን ቃል የበላይ ማድረግ ከሆነና ከዚህ ጋር አክሎም ሌላ አላማ ቢጨምርበት (ምርኮ ማግኘትን ይመስል) የኒያውን መሰረት አይጎዳውም።
ጠላቶችን ከሀገር እና ከዳር ድንበር መከላከል በአላህ መንገድ መዋጋት ውስጥ ይመደባል።
በሙጃሂዶች ዙሪያ የተጠቀሱ ትሩፋቶች የአላህን ቃል የበላይ እንዲሆን የተዋጉ ሰዎችን ብቻ የሚመለከት ነው።
التصنيفات
የጂሃድ ስነ-ስርዓት