ሰልፋችሁን አስተካክሉ! ሰልፍ ማስተካከል ሶላትን ከሚሞሉት መካከል ነውና።

ሰልፋችሁን አስተካክሉ! ሰልፍ ማስተካከል ሶላትን ከሚሞሉት መካከል ነውና።

ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሰልፋችሁን አስተካክሉ! ሰልፍ ማስተካከል ሶላትን ከሚሞሉት መካከል ነውና።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰጋጆች ሰልፋቸውን እንዲያስተካክሉ፤ ከፊላቸው ከከፊሉ እንዳይቀደምና እንዳይዘገይ አዘዙ። ሰልፍን ማስተካከል ሶላትን ከሚሞሉ ምክንያቶች አንዱ ሲሆን የሰልፍ መጣመምም ሶላት ውስጥ ጉድለትና ክፍተት የሚያስከትል መሆኑን ገለፁ።

فوائد الحديث

ሶላትን በሚያሟሉና ከጉድለት በሚያርቁ ነገሮች ላይ ሁሉ ትኩረት መስጠት መደንገጉን እንረዳለን።

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የድንጋጌው ምክንያት ግልፅ እንዲሆንና ሰዎች ለመተግበር እንዲነሳሱ ብይንን ከምክንያት ጋር ማስተሳሰራቸው የማስተማር ጥበባቸውን ያስረዳል።

التصنيفات

የኢማምና የተከታይ ህግጋት, የመስጊዶች ህግጋት