إعدادات العرض
ለወደፊት የምታወግዟቸው ጉዳዮችና አድልዎ ይከሰታል!' ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ያዙናል?' አሉ። እርሳቸውም 'በናንተ ላይ ያለባችሁን ግዴታ ትወጣላችሁ። ለናንተ ያላችሁን ሐቅ…
ለወደፊት የምታወግዟቸው ጉዳዮችና አድልዎ ይከሰታል!' ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ያዙናል?' አሉ። እርሳቸውም 'በናንተ ላይ ያለባችሁን ግዴታ ትወጣላችሁ። ለናንተ ያላችሁን ሐቅ ደግሞ ከአላህ ትጠይቃላችሁ።' አሉ።
ከኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ለወደፊት የምታወግዟቸው ጉዳዮችና አድልዎ ይከሰታል!' ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ያዙናል?' አሉ። እርሳቸውም 'በናንተ ላይ ያለባችሁን ግዴታ ትወጣላችሁ። ለናንተ ያላችሁን ሐቅ ደግሞ ከአላህ ትጠይቃላችሁ።' አሉ።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Kiswahili Português සිංහල Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá ئۇيغۇرچە Tiếng Việt ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or नेपाली Malagasy Kinyarwanda తెలుగు Lietuvių Oromoo Română മലയാളം Nederlands Soomaali Српски Українська Deutsch ಕನ್ನಡ Wolof Moore Shqip Magyar ქართული Azərbaycanالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሙስሊሞችን ገንዘብና ሌሎችንም አለማዊ ጉዳዮች በማዳላት ሙስሊሞችን በርሱ ላይ ካላቸው መብት በመከልከል እንደፈለጉ የሚያወጡ መሪዎች በሙስሊሞች ላይ እንደሚሾሙ ተናገሩ። በነርሱ ላይም የሚወገዙ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች እንደሚኖራቸው ተናገሩ። ሶሐቦችም (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና በዚህ ሁኔታ ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ጠየቁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በገንዘብ ጉዳይ ብቻቸውን መጠቀማቸው በናንተ ላይ ለነርሱ ልታሟሉ ግዴታ የሆነባችሁን ከመስማትና ከመታዘዝ እንዳይገታችሁ። ይልቁንም ታግሳችሁ መስማትና መታዘዝ ላይ አደራችሁን። በትእዛዞቻቸውም አትቃረኗቸው (አትከራከሯቸው)። እንዲያስተካክላቸው፣ ክፋታቸውንና ግፋቸውን እንዲከላከልላችሁ ለናንተ ያላችሁንም ሐቅ ከአላህ ጠይቁ!فوائد الحديث
ሐዲሡ የርሳቸውን ነቢይነት ከሚጠቁሙ ሐዲሶች መካከል አንዱ ነው። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በኡመታቸው ውስጥ የሚከሰተውን መናገራቸውና እንደተናገሩት ከመከሰቱ አንፃር ነው።
ነፍሱን ዝግጁ እንዲያደርግና ባጋጠመው ወቅት ታጋሽና ምንዳውን የሚያስብ ሊሆን ዘንድ ለተፈተነ ሰው ለወደፊት ያጋጥመዋል ተብሎ የሚታሰብ መከራን ማሳወቅ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
ከቁርአንና ሐዲሥ ጋር ያለ ትስስርን ማጠንከር ከፈተናና ልዩነት መውጫ መንገድ እንደሆነ እንረዳለን።
ለመሪዎች በመልካም ጉዳይ መስማትና መታዘዝ ላይና ግፍ እንኳ ቢያደርሱ በነርሱ ላይ አምፆ ባለመውጣት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
በፈተና ዘመን ሱናን መከተልና ጥበብን መጠቀም እንደሚገባ እንረዳለን።
አንድ ሰው በርሱ ላይ ግፍ እንኳ ቢደርስበት ባለበት እውነት ላይ መቆም እንደሚገባው እንረዳለን።
ይህ ሐዲሥ አንድ መርህን ይጠቁመናል። እርሱም፦ ከሁለት ክፋቶች ዝቅተኛውን ክፋት ይመረጣል፤ ወይም ከሁለት ጉዳቶች ቀላሉ ጉዳት ይመረጣል የሚል ነው።
التصنيفات
የመሪ ግዴታዎች