إعدادات العرض
እነዚህ ሁለቱ ከኡመቴ በወንዶቹ ላይ ክልክል ናቸው። ለሴቶቹ ግን የተፈቀደ ነው።
እነዚህ ሁለቱ ከኡመቴ በወንዶቹ ላይ ክልክል ናቸው። ለሴቶቹ ግን የተፈቀደ ነው።
ከዐሊይ ቢን አቢጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሐር በግራ እጃቸው ወርቅ በቀኝ እጃቸው በመያዝ ከዚያም እነሱን በእጃቸው ከፍ አደረጉና እንዲህ አሉ: "እነዚህ ሁለቱ ከኡመቴ በወንዶቹ ላይ ክልክል ናቸው። ለሴቶቹ ግን የተፈቀደ ነው።"»
[ሶሒሕ ነው።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî অসমীয়া Kiswahili Tiếng Việt ગુજરાતી Nederlands සිංහල پښتو ไทย नेपाली Кыргызча മലയാളം Malagasy Svenska Română తెలుగు ქართულიالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሐር ልብስ ወይም ቁራጩን በግራ እጃቸው ይዘው የወርቅ ጌጥ ወይም መሰል ነገር ደሞ በቀኝ እጃቸው ያዙና እንዲህ አሉ: ለወንዶች ሐርና ወርቅ መልበሳቸው ክልክል ነው። ለሴቶች ግን የተፈቀደ ነው።فوائد الحديث
ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: «(ክልክል) ያሉት በመልበስ መጠቀሙን ነው። ያለበለዚያማ በመመንዘር፣ በመመፅወት፣ በንግድ መጠቀሙ ለሁሉም ፆታ የተፈቀደ ነው። ወርቅን በእቃ መልክ ማድረግና በእቃ መልክ አድርጎ መጠቀሙ ደግሞ ለሁሉም ፆታ ክልክል ነው።»
የእስልምና ሸሪዓ ሴቶች ማጌጥና የመሳሰሉትን ከመፈለጋቸው አንፃር ህጉን ለነሱ ሰፋ እንዳደረገላቸው እንረዳለን።
التصنيفات
ልብስና ጌጥ