إعدادات العرض
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ የጉዳይ ጊዜ ኹጥባን (ኹጥበቱል ሓጃህ) አስተማሩን
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ የጉዳይ ጊዜ ኹጥባን (ኹጥበቱል ሓጃህ) አስተማሩን
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ የጉዳይ ጊዜ ኹጥባን (ኹጥበቱል ሓጃህ) አስተማሩን: 'ኢነልሐምደ ሊላህ ነስተዒኑሁ ወነስተጝፊሩሁ ወነዑዙ ቢላሂ ሚን ሹሩሪ አንፉሲና ፤ መን የህዲላሁ ፈላሙዺለ ለሁ ወመንዩዽሊል ፈላ ሃዲየ ለሁ ፤ ወአሽሀዱ አን ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአሽሀዱ አነ ሙሓመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ ሱረቱ ኒሳእ: 1፣ ኣሊ‐ዒምራን: 102፣ አል‐አሕዛብ: 70‐71'" (ትርጉሙም: ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው። እገዛን ከርሱ እንፈልጋለን። ምህረትንም ከርሱ እንፈልጋለን። ከነፍሳችን ክፋትም በርሱ እንጠበቃለን። አላህ የመራው ሰው አጥማሚ የለውም። ያጠመመውንም መሪ የለውም። ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ። ሙሐመድም የአላህ ባሪያውና መልክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ። {እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን (ሐዋን) የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ። ያንንም በርሱ የምትጠያየቁበትን አላህንና ዝምድናዎችንም (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ። አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና።} [አንኒሳእ: 1] {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢውን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት። እናንተም ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጂ አትሙቱ።} [አሉ ዒምራን: 102] {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ። ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ። [70] ሥራዎቻችሁን ለእናንተ ያበጅላችኋልና ሀጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምርላችኋል። አላህንና መልክተኛውን የሚታዘዝም ሰው በእርግጥ ታላቅን እድል አገኘ። [71]} [አልአሕዛብ 70 -71])
الترجمة
العربية Bosanski English فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو हिन्दी 中文 বাংলা Español Kurdî Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் සිංහල မြန်မာ ไทย 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە Hausa دری Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy Kinyarwanda नेपाली Română Српски Soomaali Deutsch Moore Українська Български Tagalog Wolof Azərbaycanالشرح
ኢብኑ መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የጉዳይ ጊዜ ኹጥባን እንዳስተማሯቸው ተናገሩ። ይህም እንደጋብቻና የጁመዓ ኹጥባ በመሰሉ ኹጥባዎችና በጉዳዮቻቸው ወቅት ንግግርን ሲጀምሩ የሚባል ነው። ይህቺ ኹጥባ አጠቃላይ የምስጋና አይነቶች አላህ እንደሚገባው፣ አጋር ከሌለው ከርሱ ብቻ እገዛን መፈለግን፣ ወንጀሎችን መሸሸግና ይቅር ማለትን ከርሱ መፈለግን፣ ከነፍስ ክፋትና ከሌሎችም ሁሉ ክፋቶች ወደርሱ መጠጋትንና ሌሎችንም ትላልቅ ሀሳቦችን ሰብስባለች። ቀጥለውም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መመራት በአላህ እጅ መሆኑን ፤ አላህ የመራውን ሰው አጥማሚ እንደሌለው ያጠመመውንም መሪ እንደሌለው ተናገሩ። ቀጥለውም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም የሚለውን የተውሒድን የምስክር ቃልና ሙሐመድ የአላህ ባሪያና መልክተኛ ናቸው የሚለውን የመልክተኝነትን ምስክር ቃል ጠቀሱ። ይህንንም ኹጥባ የአላህን ፊት ፈልጎ የአላህን ትእዛዛት በመፈፀምና ክልከላውን በመራቅ አላህን በመፍራት የሚያዝ እንዲሁም ይህንን የፈፀመ ሰውም ምንዳው ስራውና ንግግሩ ይስተካከላል፣ ወንጀሎቹ ይማራሉ፣ ሀጢአቶቹ ይረግፋሉ፣ በዱንያም ያማረ ህይወት ይጎናፀፋል፣ የትንሳኤ ቀንም በጀነት ስኬትን ይቀዳጀል። የሚልን ሀሳብ በጠቀለሉ እነዚህ ሶስት አንቀፆች ቋጩት።فوائد الحديث
የጋብቻን የጁመዓንና ሌሎችንም ኹጥባዎች በዚህ ኹጥባ መክፈት እንደሚወደድ እንረዳለን።
አንድ ኹጥባ ምስጋናን ፣ ሁለቱን የምስክር ቃላቶችንና ጥቂት የቁርአን አንቀጾችን ያካተተ መሆን ይገባዋል።
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለባልደረቦቻቸው ለእምነታቸው የሚያስፈልጋቸውን ማስተማራቸውን እንረዳለን።
التصنيفات
የጋብቻ መስፈርቶችና ህግጋት