የሚያጠራጥርህን ነገር ተውና ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ!

የሚያጠራጥርህን ነገር ተውና ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ!

የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የልጅ ልጅና መአዛቸው ከሆነው ከአቡ ሙሐመድ ሐሰን ቢን ዓሊይ ቢን አቢጧሊብ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ይህንን ሸምድጃለሁ: "የሚያጠራጥርህን ነገር ተውና ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ!"

[ሶሒሕ ነው።] [رواه الترمذي والنسائي]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ክልክል ነው ወይስ አይደለም፣ ሐላል ነው ወይስ ሐራም ነው እያልክ የምትጠራጠርበት ንግግርና ተግባር በመተው መልካምነቱንና ፍቁድነቱን እርግጠኛ ወደሆንክበትና ወዳልተጠራጠርክበት መሄድን አዘዙ።

فوائد الحديث

ሙስሊም የሆነ ሰው ጉዳዮቹን በርግጠኝነት ላይ መመስረት አለበት። የሚጠራጠርበትን ነገር ትቶ በሃይማኖቱም እውቀት ላይ መሆን አለበት።

አጠራጣሪ ነገር ላይ ከመውደቅ መከልከሉን እንረዳለን።

እርጋታና እረፍትን ከፈለግክ አጠራጣሪ ነገርን ትተህ ወደ ጎን መጣል አለብህ።

አላህ ለባሮቹ ነፍሳቸውና ሀሳባቸው እረፍት የሚያገኝበትን ማዘዙና ጭንቀትና መዋለል ውስጥ ከሚከታቸው ነገርም መከልከሉ ለነርሱ ያለውን እዝነት ያስረዳናል።