إعدادات العرض
እነሆ በናንተ ላይ መሪዎች ይሾማሉ። የምታውቁትንም የምታወግዙትንም ስራ ይሰራሉ። (የሚሰሩትን ውግዝ ስራ) የጠላ ሰው (ከወንጀል) ጠራ። ያወገዘም ሰው ሰላም ሆነ። ነገር ግን (የነሱን…
እነሆ በናንተ ላይ መሪዎች ይሾማሉ። የምታውቁትንም የምታወግዙትንም ስራ ይሰራሉ። (የሚሰሩትን ውግዝ ስራ) የጠላ ሰው (ከወንጀል) ጠራ። ያወገዘም ሰው ሰላም ሆነ። ነገር ግን (የነሱን ውግዝ ተግባር) የወደደና የተከተለ (ወንጀል ውስጥ ወደቀ)
ከኡሙ ሰለማ ኡሙል ሙእሚኒን (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "እነሆ በናንተ ላይ መሪዎች ይሾማሉ። የምታውቁትንም የምታወግዙትንም ስራ ይሰራሉ። (የሚሰሩትን ውግዝ ስራ) የጠላ ሰው (ከወንጀል) ጠራ። ያወገዘም ሰው ሰላም ሆነ። ነገር ግን (የነሱን ውግዝ ተግባር) የወደደና የተከተለ (ወንጀል ውስጥ ወደቀ)" ሶሓቦችም "ታዲያ አንዋጋቸውምን?" ብለው ጠየቁ። ነቢዩም "ሶላትን እስከሰገዱ ድረስ በፍፁም (እንዳትዋጓቸው!)" ብለው መለሱ።
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá සිංහල தமிழ் ไทย دری Кыргызча or Kinyarwanda नेपाली Română Malagasy Lietuvių Oromoo Nederlands Soomaali Српски Українська ಕನ್ನಡ Wolof Mooreالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በኛ ላይ መሪዎች እንደሚሾሙና ከፊል ስራዎቻቸው ከሸሪዓ ጋር የተስማማ ስለሆነ መልካም እንደምንለውና፤ ከፊሉን ደግሞ ከሸሪዓ ጋር ስለሚፃረር እንደምናወግዘው ተናገሩ። ውግዝ ተግባሮቻቸውን ማውገዝ ያልቻለና በቀልቡ የጠላ ሰው በርግጥም ከወንጀልና ንፍቅና ጠራ። በእጁ ወይም በአንደበቱ ማውገዝ የቻለ ሰውና በነርሱ ላይ ይህንን ያወገዘ በርግጥ ከወንጀልና ከወንጀል ተባባሪነት ሰላም ሆኗል። ነገር ግን ድርጊታቸውን የወደደና በርሱ ላይ የተከተላቸው እነርሱ እንደጠፉት ይጠፋል። ከዚያም ሶሐቦች ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ይህን አይነት ባህሪ የተላበሱ መሪዎችን አንዋጋምን?" ብለው ጠየቁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "በመካከላችሁ ሶላትን ቀጥ አድርገው እስከሰገዱ ድረስ በፍፁም እንዳትዋጓቸው!" በማለት ከዚህ ከለከሏቸው።فوائد الحديث
ለወደፊት የሚከሰቱ ሩቅ ነገሮችን መናገራቸውና እንደተናገሩት መከሰቱ የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነቢይነት ከሚጠቁሙ ነገሮች መካከል አንዱ ነው።
ውግዝ ተግባርን መውደድና በርሱ ላይ መተባበር አይፈቀድም። ውግዝን ማውገዝም ግዴታ ነው።
መሪዎች ከሸሪዓ የተፃረረን ነገር የፈጠሩ ጊዜ በዚህ ላይ እነርሱን መታዘዝ አይፈቀድም።
በሙስሊም መሪዎች ላይ አምፆ መውጣት ያልተፈቀደው ይህን ተከትሎ ብክለት፣ ደም መፋሰስና የደህንነት ቀውስ ስለሚከሰት ነው። የወንጀለኛ መሪዎችን ውግዝ ተግባር መቻልና አስቸጋሪነታቸውን መታገስ ከነዚህ ነገሮች አንፃር እጅግ ቀላል ነው።
ሶላት ጉዳዩዋ (ደረጃዋ) ትልቅ ነው። ሶላት በክህደትና ኢስላም መካከል የምትለይ መሆኗን እንረዳለን።
التصنيفات
በመሪ ላይ ማመፅ