إعدادات العرض
1- ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር መሪያችንን በችግርም ጊዜ ሆነ በድሎት ፣ በንቃትም ጊዜ ሆነ በጠላንበትም ጊዜ ፣ በኛ ላይ አድሎ ቢደረግብንም እንኳ እንድንሰማውና እንድንታዘዘው
2- እነሆ በናንተ ላይ መሪዎች ይሾማሉ። የምታውቁትንም የምታወግዙትንም ስራ ይሰራሉ። (የሚሰሩትን ውግዝ ስራ) የጠላ ሰው (ከወንጀል) ጠራ። ያወገዘም ሰው ሰላም ሆነ። ነገር ግን (የነሱን ውግዝ ተግባር) የወደደና የተከተለ (ወንጀል ውስጥ ወደቀ)
3- ከመሪ ትእዛዝ አምፆ በመውጣት የሙስሊሙን ህብረት ተለይቶ የሞተ የድንቁርና አሟሟት ሙቷል።
4- ጉዳያችሁ በአንድ መሪ የተሰበሰበ ሁኖ ሳለ አንድነታችሁን ሊሰነጥቅ ወይም ህብረታችሁን ሊበታትን የመጣ ሰውን ግደሉት።