إعدادات العرض
ጉዳያችሁ በአንድ መሪ የተሰበሰበ ሁኖ ሳለ አንድነታችሁን ሊሰነጥቅ ወይም ህብረታችሁን ሊበታትን የመጣ ሰውን ግደሉት።
ጉዳያችሁ በአንድ መሪ የተሰበሰበ ሁኖ ሳለ አንድነታችሁን ሊሰነጥቅ ወይም ህብረታችሁን ሊበታትን የመጣ ሰውን ግደሉት።
ከዐርፈጀህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻዋለሁ: "ጉዳያችሁ በአንድ መሪ የተሰበሰበ ሁኖ ሳለ አንድነታችሁን ሊሰነጥቅ ወይም ህብረታችሁን ሊበታትን የመጣ ሰውን ግደሉት።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Bosanski English فارسی Français Русский اردو हिन्दी Bahasa Indonesia 中文 বাংলা ئۇيغۇرچە Español Kurdî Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் සිංහල မြန်မာ ไทย 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands Türkçe Hausa دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली Italiano or ಕನ್ನಡ Oromoo Română Soomaali Српски Wolof Українська Tagalog Moore Malagasy Azərbaycan ქართული Magyarالشرح
ሙስሊሞች በአንድ መሪና በአንድ ህብረት የተሰበሰቡ ሆነው ሳለ ከዚያም መሪነቱን መገዳደር ፈልጎ ወይም ሙስሊሞችን ከአንድ ህብረት በላይ እንዲሆኑ መበታተን ፈልጎ የመጣን ሰው አደጋውን ለመከላከልና የሙስሊሞችን ደም ለመጠበቅ ሲባል በነርሱ ላይ መከልከልና መጋደል ግዴታ እንደሆነ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ።فوائد الحديث
ከወንጀል ውጪ በሆኑ ጉዳዮች የሙስሊሞችን መሪ መስማትና መታዘዝ ግዴታ መሆኑን እና በርሱ ላይ አምፆ መውጣትም ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
የሙስሊሞች መሪ ላይና ህብረታቸው ላይ አምፆ የወጣ ሰውን ክብሩና ዘሩ ምንም ያህል የላቀ ቢሆን እንኳ እሱን መዋጋት ግዴታ ነው።
በአንድነትና አለመለያየት፣ አለመበታተን ላይ መነሳሳቱን (መበረታታቱን) እንረዳለን።
التصنيفات
በመሪ ላይ ማመፅ