إعدادات العرض
ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር መሪያችንን በችግርም ጊዜ ሆነ በድሎት ፣ በንቃትም ጊዜ ሆነ በጠላንበትም ጊዜ ፣ በኛ ላይ አድሎ ቢደረግብንም…
ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር መሪያችንን በችግርም ጊዜ ሆነ በድሎት ፣ በንቃትም ጊዜ ሆነ በጠላንበትም ጊዜ ፣ በኛ ላይ አድሎ ቢደረግብንም እንኳ እንድንሰማውና እንድንታዘዘው
ከዑባዳህ ቢን ሷሚት (ረዲየላሁ ዐንሁ) አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው እንዲህ አለ፦ "ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር መሪያችንን በችግርም ጊዜ ሆነ በድሎት ፣ በንቃትም ጊዜ ሆነ በጠላንበትም ጊዜ ፣ በኛ ላይ አድሎ ቢደረግብንም እንኳ እንድንሰማውና እንድንታዘዘው፤ የስልጣን ባለቤትም በጉዳዩ ከአላህ ግልፅ ማስረጃ የመጣበትን ግልፅ ክህደት እስካላያችሁበት ድረስ (ስልጣኑን) ላንጋፋው፣ የትም ብንሆን እውነትን እንድንናገር ፣ በአላህ መንገድም የወቃሽን ወቀሳ ላንፈራ ቃል ተጋብተናል።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands සිංහල Hausa ไทย دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली Malagasy Italiano or ಕನ್ನಡ Oromoo Română Soomaali Српски Wolof Українська Moore Azərbaycan ქართული Magyarالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሶሐቦች ጋር ለመሪዎችና አስተዳዳሪዎች በገርም ይሁን በከባድ፣ በሀብትም ይሁን በድህነት ወቅት፣ ትእዛዞቻቸው ነፍስ የምትወደውም ሆነ የምትጠላው ለነርሱ ታዛዥ እንዲሆኑ ቃል ኪዳን ፈፀሙ። መሪዎች በህዝብ አጠቃላይ ገንዘብ ወይም በማእረግ ወይም ከዚህ ውጪ ባሉ ነገሮች አድሎ ቢፈፅሙ እንኳ መሪዎችን በመልካም መታዘዝና መስማት ግዴታ መሆኑንና እነርሱንም አምፀው ላይወጡ ቃል ኪዳን ፈፀሙ። ምክንያቱም መሪዎችን በመዋጋት የሚመጣው ፈተናና ብልሽት በግፋቸው ሳቢያ ከሚከሰተው ብልሽት እጅግ የገዘፈ ነውና። በንግግራቸው ለአላህ ብቻ ያጠሩ (ሙኽሊስ) ሲሆኑና ወቃሻቸውን ሳይፈሩ እውነትን በማንኛውም ስፍራ መናገርም ሌላው ቃል ኪዳን የተጋቡት ጉዳይ ነው።فوائد الحديث
መሪዎችን የመስማትና የመታዘዝ ዋናው ጥቅም የሙስሊሞችን ቃል አንድ ማድረግና ልዩነትን ማስወገድ ነው።
አላህን ከመወንጀል ውጪ በድሎትም ይሁን በችግር፣ በንቃትም ጊዜ ይሁን በጠላንበት፣ እኛ ላይ አድሎ በሚያደርጉብን ወቅትም ቢሆን መሪዎችን መስማትና መታዘዝ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
በአላህ ጉዳይ የወቃሽን ወቀሳ ሳንፈራ እውነትን የትም ብንሆን መናገር ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።