‹የሚያጠራጥርህን ነገር ተውና ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት እርጋታን የተላበሰ ነው። ውሸት ደሞ ጥርጣሬን የተላበሰ ነው።›

‹የሚያጠራጥርህን ነገር ተውና ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት እርጋታን የተላበሰ ነው። ውሸት ደሞ ጥርጣሬን የተላበሰ ነው።›

ከአቡል ሐውራእ አስሰዕዲይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: ለሐሰን ቢን ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - «ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምን ሸምድደሃል? አልኩት። እርሱም: "ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህን ሸምድጃለሁ አለኝ። ‹የሚያጠራጥርህን ነገር ተውና ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት እርጋታን የተላበሰ ነው። ውሸት ደሞ ጥርጣሬን የተላበሰ ነው።›"»

[ሶሒሕ ነው።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ክልክል ነው ወይስ አይደለም፣ ሐላል ነው ወይስ ሐራም ነው እያልክ የምትጠራጠርበት ንግግርና ተግባር በመተው መልካምነቱንና ፍቁድነቱን እርግጠኛ ወደሆንክበትና ወዳልተጠራጠርክበት መሄድን አዘዙ። ቀልብ እርግጠኛ በሆነበት ነገር ላይ ይረጋል። አጠራጣሪ በሆነ ነገር ደግሞ ይወዛገባል።

فوائد الحديث

ሙስሊም የሆነ ሰው ጉዳዮቹን በርግጠኝነት ላይ መመስረት አለበት። የሚጠራጠርበትን ነገር ትቶ በሃይማኖቱም እውቀት ላይ መሆን አለበት።

አጠራጣሪ ነገር ላይ ከመውደቅ መከልከሉን እንረዳለን።

እርጋታና እረፍትን ከፈለግክ አጠራጣሪ ነገርን ትተህ ወደ ጎን መጣል አለብህ።

አላህ ለባሮቹ ነፍሳቸውና ሀሳባቸው እረፍት የሚያገኝበትን ማዘዙና ጭንቀትና መዋለል ውስጥ ከሚከታቸው ነገርም መከልከሉ ለነርሱ ያለውን እዝነት ያስረዳናል።

التصنيفات

መጣረስና ሚዛን የደፋውን መግለፅ