إعدادات العرض
ማነብነብ (ሩቃ) ፣ ሂርዝ ማንጠልጠልና መስተፋቅር ሽርክ ናቸው።
ማነብነብ (ሩቃ) ፣ ሂርዝ ማንጠልጠልና መስተፋቅር ሽርክ ናቸው።
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህን መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "ማነብነብ (ሩቃ) ፣ ሂርዝ ማንጠልጠልና መስተፋቅር ሽርክ ናቸው።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Français Kurdî Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் සිංහල မြန်မာ Русский Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە Hausa ไทย دری Fulfulde Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių or Română Kinyarwanda Српски O‘zbek Moore नेपाली Malagasy тоҷикӣ Oromoo Wolof Soomaali Български Українська Azərbaycan ქართული bm lnالشرح
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ማድረጉ ሺርክ የሆኑ ሁኔታዎችን ገለፁ። ከነሱም መካከል: - አንደኛ: ማነብነብ (ሩቃ) :- ይህም የጃሂሊያ ሰዎች ይታከሙበት የነበረውን ሽርክን የሰበሰበ ንግግር ነው። ሁለተኛ: በጨሌና በመሳሰሉ የተሰሩ ሂርዞችን ማንጠልጠል: ይህም የሰው አይን እንዲከላከል በህፃናት፣ በእንስሶችና በሌሎችም ላይ የሚንጠለጠል ነው። ሶስተኛ: መስተፋቅር: ይህም ከሁለቱ ጥንዶች መካከል አንዱ ሌላኛውን እንዲያፈቅር ተደርጎ የሚሰራ ነው። እነዚህ ነገሮች ከሺርክ የሚመደቡ ናቸው። ምክንያቱም ይህ በማስረጃ የፀና ሸሪዓዊ ሰበብም ያልሆነን በተለምዶ የተረጋገጠ ህዋሳዊ ሰበብም ያልሆነን ሰበብ አድርጎ መያዝ ነውና። እንደ ቁርአን መቅራት የመሰለ ሸሪዐዊ ሰበቦችን መጠቀም ወይም በተለምዶ የተረጋገጡ መድሃኒቶችን የመሰለ ህዋሳዊ ሰበቦችን መጠቀም ግን መጥቀምና መጉዳት በአላህ እጅ መሆኑንና እነሱ ሰበብ ብቻ መሆናቸውን ከማመን ጋር እስከሆነ ድረስ መጠቀም ይፈቀዳል።فوائد الحديث
ተውሒድና ዐቂዳችንን ከሚያጎድላቸው ነገር መጠበቅ እንደሚገባ ፤
ሽርካዊ ማነብነቦችን፣ ሂርዝና መስተፋቅርን መጠቀም ክልክል መሆኑን ፤
እነዚህን ሶስት ነገሮች እንደ ሰበብ አድርጎ ማመን ትንሹ ሺርክ ነው። ምክንያቱም ሰበብ ያልሆነን ነገር ሰበብ ማድረግ ነውና። ነገር ግን (ከሰበብም በላይ) በራሷ ትጠቅማለችም ትጎዳለችም ብሎ ካመነ ትልቁ ሺርክ ነው።
ክልክል የሆኑ ሺርካዊ ሰበቦችን መፈፀም መከልከሉን ፤
ሸሪዐዊ ከሆነው ሩቃ በስተቀር ማነብነብ ሺርክ ስለሆነ መከልከሉን ፤
ቀልብ በአላህ ላይ ብቻ ነው ሊንጠለጠል የሚገባው ፤ ጉዳትም ይሁን ጥቅም የሚገኘው አጋር ከሌለው ከሱ ብቻ ነውና። ከአላህ ውጪ መልካምን የሚያመጣ የለም ፤ ከአላህ ውጪ መጥፎን የሚከላከልም የለም።
የሚፈቀደው ሩቃ ሶስት መስፈርቶችን ያካተተ መሆን ይገባዋል: 1- ሩቃው ሰበብ ብቻ እንደሆነና ከአላህ ፍቃድ ውጪ እንደማይጠቅም ማመን፤ 2 - ሩቃው በቁርአን፣ በአላህ ስሞችና ባህሪያት ፣ በነቢያዊ ዱዓዎች፣ ሸሪዐውን በጠበቁ ዱዓዎች ሊሆን ይገባዋል፤ 3 - ሩቃው በግልፅ ቋንቋ ሊሆን ይገባል። የማይገቡ በሆኑ ቋንቋ የሚሰመሩ መስመሮችና ማታለያዎችን የራቀ ሊሆን ይገባል።
التصنيفات
ሸሪዓዊ ሩቃ