ስንፍናና ጮሌነት ወይም ጮሌነትና ስንፍና ሳይቀር ሁሉ ነገር በአላህ ውሳኔ ነው።

ስንፍናና ጮሌነት ወይም ጮሌነትና ስንፍና ሳይቀር ሁሉ ነገር በአላህ ውሳኔ ነው።

ጣዉስ እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ባለደረቦች የሆኑ ሰዎችን አግኝቻለሁ። "ሁሉም ነገር በአላህ ውሳኔ ነው"ይሉም ነበር። ጣዉስ እንዲህም አሉ፦ " ዐብደላህ ቢን ዑመርን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ስንፍናና ጮሌነት ወይም ጮሌነትና ስንፍና ሳይቀር ሁሉ ነገር በአላህ ውሳኔ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁሉም ነገር በአላህ ውሳኔ መሆኑን ገለፁ። ስንፍና ሳይቀር ተወስኗል: እሱም: - ዱንያዊና አኺራዊ ከሆኑ ጉዳዮች መስራት ግድ የሆነበትን ነገር መተው፣ ሳይሰሩ መገኘት ፣ ከወቅቱ ማዘግየት ነው። ጮሌነት ሳይቀር ተወስኗል: እሱም:- ዱንያዊና አኺራዊ ጉዳዮችን ለመስራት መነቃቃትና ብልህ መሆን ማለት ነው። የላቀውና የተከበረው አላህ ስንፍናና ጮሌነትን ሳይቀር ሁሉንም ነገር ወስኗል። በዚህ ዓለም የአላህ ዕውቀትና ፍላጎት የቀደመው ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አይከሰትም።

فوائد الحديث

በአላህ ውሳኔ (ቀደር) ጉዳይ የሰሐቦች -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እምነት መገለፁ።

ስንፍናና ንቁነት ሳይቀር ሁሉም ነገር የሚከሰተው በአላህ ውሳኔ መሆኑን፤

የአላህ መልክተኛን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሐዲሥ በማስተላለፉ ረገድ የሰሐቦች -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- ጥንቃቄና ማረጋገጥ፤

በመልካሙም ሆነ በመጥፎው ሁሉም ጉዳይ በአላህ ውሳኔ መሆኑን ማመንን ተረድተናል።

التصنيفات

በአላህ ፍርድና ውሳኔ ማመን, የቀዷና ቀደር ደረጃዎች