إعدادات العرض
ሰዎች ግፈኛን ተመልክተው እጁን ካልያዙት አላህ ከርሱ በሆነ ቅጣት ሊያጠቃልላቸው ይቀርባል።
ሰዎች ግፈኛን ተመልክተው እጁን ካልያዙት አላህ ከርሱ በሆነ ቅጣት ሊያጠቃልላቸው ይቀርባል።
ከአቡበከር አስሲዲቅ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «እናንተ ሰዎች ሆይ! {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁን (ከእሳት) ያዙ! (ጠብቁ)። በተመራችሁ ጊዜ የተሳሳተ ሰው አይጎዳችሁም።} የሚለውን አንቀፅ ታነቡታላችሁ። እኔ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "ሰዎች ግፈኛን ተመልክተው እጁን ካልያዙት አላህ ከርሱ በሆነ ቅጣት ሊያጠቃልላቸው ይቀርባል።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Kiswahili Português සිංහල Tiếng Việt دری অসমীয়া ไทย Svenska Кыргызча Yorùbá ગુજરાતી नेपाली മലയാളം Oromoo Română Nederlands Soomaali پښتو తెలుగు Kinyarwanda Malagasy ಕನ್ನಡ Српски Mooreالشرح
አቡበከር አስሲዲቅ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሰዎች ይህቺን አንቀፅ እንደሚያነቡ ተናገሩ: {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁን (ከእሳት) ያዙ! (ጠብቁ)። በተመራችሁ ጊዜ የተሳሳተ ሰው አይጎዳችሁም።} [አልማኢዳህ: 105] ከዚህም አንቀፅ የሰው ልጅ ያለበት ግዴታ ነፍሱን በማስተካከል ላይ መልፋት ብቻ እንደሆነ፤ ነፍሱን ካስተካከለም የጠመመ ቢጠም ምንም እንደማይጎዳቸው፣ በመልካም በማዘዝና ከመጥፎ በመከልከል ዙሪያ እንደማይጠየቁ ይረዳሉ። ይህ ግን (እነሱ እንዳሰቡት) አለመሆኑን ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ እንደሰማቸው በመንገር አሳወቃቸው: ሰዎች ግፈኛን ተመልክተው በመከልከል ላይ አቅሙ እያላቸው ከግፉ ካልከለከሉት አላህ መጥፎውን የሰራውንም ሆነ አይቶ ዝም ያለውን ሁሉንም እርሱ ዘንድ ባለ ቅጣት ሊጠቀልላቸው ይቀርባል።فوائد الحديث
የሙስሊሞች ግዴታ መመካከር፣ ወደ መልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ነው።
የአላህ አጠቃላይ ቅጣት ግፈኛን በግፉ ሲያካትተው መጥፎን እያየ በዚህ መጥፎ ነገር ላይ ማውገዝ እየቻለ ዝም ያለንም ያካትታል።
ለአጠቃላዩ ማህበረሰብ ቁርአናዊ አንቀጾችን በትክክለኛው መንገድ ማስተማርና ማስገንዘብ እንደሚገባ እንረዳለን።
አላህ ባልገለፀው መልኩ መገንዘብ ውስጥ እንዳይወድቅ የአላህን መጽሐፍ ለመገንዘብ ትኩረት መስጠት በሁሉም የሰው ልጅ ላይ ግዴታ ነው።
መመራት በመልካም ማዘዝንና ከመጥፎ መከልከልን ከመተው ጋር አይረጋገጥም።
የአንቀፁ ትክክለኛ ትርጉም: ነፍሳችሁን ከወንጀል በመጠበቅ ላይ ያዙ! ነፍሳችሁን ከጠበቃችሁ በኋላ ከመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ሲሳናችሁ ክልክሎቹን እስካልተዳፈራችሁ ድረስ የጠመመ ሰው በመዳፈሩ ምንም አይጎዳችሁም።
التصنيفات
በመልካም የማዘዝና ከመጥፎ የመከልከል ፍርድ