إعدادات العرض
አላህ እንዲህ ብሏል 'የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ላንተም ይሰጥሃል!'
አላህ እንዲህ ብሏል 'የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ላንተም ይሰጥሃል!'
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ እንዲህ ብሏል 'የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ላንተም ይሰጥሃል!'"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు မြန်မာ ไทย Deutsch 日本語 پښتو অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە Kiswahili தமிழ் دری Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy Română Kinyarwanda नेपाली Српски Soomaali Moore Українська Български Wolof Azərbaycan ქართული тоҷикӣ bm Oromoo Македонскиالشرح
ከፍ ያለውና የላቀው አላህ "የአደም ልጅ ሆይ! ግዴታም ይሁን ተወዳጅ የሆኑብህን ወጪዎች ለግስ! ላንተም ሲሳይን አሰፋልሃለሁ፣ ያዋጣኸውን ወጪ ልውጫ እሰጥሃለሁ፣ በሰጠሁህም ነገር ላንተ እባርክልሃለሁ" ማለቱን ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።فوائد الحديث
በአላህ መንገድ መስጠትና መመፅወት መበረታታቱን እንረዳለን።
መልካም በሆኑ መንገዶች ላይ ወጪ ማድረግ ሲሳያችን በረከት እንዲያገኝና እንዲባዛ ከሚያደርጉ እንዲሁም ሰውዬው ያወጣውን ወጪ አላህ እንዲተካለት ከሚያደርጉ ትልልቅ ምክንያቶች መካከል ነው።
ይህ ሐዲሥ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጌታቸው ከሚያስተላልፉት ሐዲሥ መካከል አንዱ ነው። ሐዲሠል ቁድሲይ ወይም ሐዲሠል ኢላሂይ በመባል ይጠራል። ቃሉም ሀሳቡም ከአላህ ሲሆን ነገር ግን ቁርአን ከሌሎች የተለየበት የሆኑ በማንበቡ (በየፊደላቱ ሐሰና የሚያስገኘውን) አምልኮን መፈፀም፣ እሱን ለማንበብ ውዱእ ማድረግና አምሳያውን ማንም እንደማያመጣ መነገሩ፣ ተአምራዊነቱና ከዚህም ውጪ ያሉ የቁርአን መለዮዎችን አልያዘም።