إعدادات العرض
የመጽሐፍ ባለቤቶች (በሚተረጉሙላችሁ) አትመኑዋቸውም አታስተባብሏቸውም {በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርአን) አመንን………} በሉ።
የመጽሐፍ ባለቤቶች (በሚተረጉሙላችሁ) አትመኑዋቸውም አታስተባብሏቸውም {በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርአን) አመንን………} በሉ።
አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ "የመጽሐፉ ባለቤቶች ለሙስሊሞች ተውራትን በይብራይስጠኛ እያነበቡ ወደ ዐረብኛ ይተረጉሟት ነበር። የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "የመጽሐፍ ባለቤቶች (በሚተረጉሙላችሁ) አትመኑዋቸውም አታስተባብሏቸውም {በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርአን) አመንን………} በሉ። [አልበቀራህ: 136]"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Español Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe Bosanski සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa മലയാളം తెలుగు Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া Shqip دری Ελληνικά Български Fulfulde Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy Română Kinyarwanda Српски тоҷикӣ O‘zbek नेपाली Moore Kurdî Wolof Soomaali Français Oromoo Azərbaycan Tagalog Українська தமிழ் bm Deutsch ქართული Português Македонски Magyar Lingala Русский 中文الشرح
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የመጽሐፍ ባለቤቶች ከመጽሐፎቻቸው በሚያወሩት ነገር ከመሸወድ ኡመታቸውን አስጠነቀቁ። ይህም በነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ዘመን አይሁዶች ተውራትን በይብራይስጠኛ ቋንቋ (የአይሁዶች ቋንቋ ነው) እያነበቡ ወደ ዐረብኛ ይተረጉሙት ነበር። ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ "የመጽሐፍ ባለቤቶችን አትመኑዋቸውም አታስተባብሏቸውም" ይህ ግን እውነተኝነቱ ከውሸቱ ባልታወቀበት ጉዳይ ነው። ይህንንም ያሉበት አላህ ወደኛ በወረደው ቁርኣንና ወደነርሱ በወረደው መጽሐፍ እንድናምን ስላዘዘን ነው። ነገር ግን እነሱ ከነዚህ መጽሐፎቻቸው እያጣቀሱ የሚተርኩትን ጉዳዮች በሸሪዐችን እውነተኛውን ከውሸተኛው የሚገልፅልን ስላልተቀመጠ ጤነኛውን ከበሽተኛው ለይተን የምናውቅበት መንገድ የለም። ስለዚህ ፍርድ ከመስጠት እንታቀባለን። መጽሐፉን በመበረዛቸው ላይ እንዳንጋራቸው አናምናቸውም። አላህ እንድናምነው ያዘዘን የሆነን ትክክለኛ ነገር አውርተው ያወገዘ ሰው እንዳንሆንም አናስተባብላቸውም። ስለዚህ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ እንድንል አዘዙን። {"በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርኣን) ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሓቅም ወደ ያዕቆብና ወደ ነገዶቹም በተወረደው በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለርሱ (ለአላህ) ታዛዦች ነን" በሉ።} [አልበቀራህ: 136]فوائد الحديث
የመጽሐፍ ባለቤቶች የተናገሯቸው ጉዳዮች ሶስት ክፍሎች ናቸው።
አንዱ ክፍል: ቁርኣንና ሐዲሥን የሚገጥም የሆነ ነው ይህም እናምንበታለን። ሁለተኛው ክፍል: ቁርኣንና ሐዲሥን የሚቃረን ሲሆን ይህም ጥመትና የሚስተባበል ነው። ሦስተኛው ክፍል: በቁርኣንም ሆነ በሐዲሥ ውስጥ እውነተኝነቱንም ስህተቱንም የሚጠቁም አልተገለፀም። ይህ ይወራል ነገር ግን አይታመንበትምም አይስተባበልም።