‹ቢላል ሆይ! ሶላትን ኢቃም ብለህ በሶላት እረፍት ስጠን።›'

‹ቢላል ሆይ! ሶላትን ኢቃም ብለህ በሶላት እረፍት ስጠን።›'

ከሳሊም ቢን አቢ ጀዕድ እንደተዘገበው እንዲህ አሉ: "አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ: 'ምናለ ሰግጄ እረፍት ባገኘሁ።' አለ። ሰዎቹ በዚህ ንግግሩ ላይ ያነወሩት መስሎ ሲታይም እንዲህ አለ: 'የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: ‹ቢላል ሆይ! ሶላትን ኢቃም ብለህ በሶላት እረፍት ስጠን።›'"

[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ ዘግበውታል።]

الشرح

ከሶሐቦች መካከል አንዱ "ምናለ ሰግጄ እረፍት ባገኘሁ።" አለ። በዙሪያው ያሉ ሰዎች በዚህ ንግግሩ ላይ ያነወሩት መሰሉ። በዚህ ጊዜም እንዲህ አለ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: 'ቢላል ሆይ! የሶላትን አዛንና ኢቃም አድርግ በርሷ እረፍት እንድናገኝ!'" ይህም ሶላት ውስጡ አላህን ማናገር፣ ለነፍስና ለቀልብ እርካታ ስላለው ነው።

فوائد الحديث

ሶላት ውስጥ አላህን ማናገር ስላለ የቀልብ እርካታ የሚገኘው በሶላት ነው።

አምልኮ መፈፀም በከበደው ላይ መወገዙን እንረዳለን።

ያለበትን ግዴታ የተወጣና ጫንቃውን ካለበት ግዴታ ያጠራ በዚህ እርካታና የእረፍት ስሜትን ያገኛል።

التصنيفات

የሶላት ትሩፋት, አዛንና ኢቃማህ