إعدادات العرض
አላህ አንድ ሀላፊነት ላይ ሹሞት የተሰጠውን ሀላፊነት የሚያታልል ሆኖ የሚሞት ባሪያ የለም አላህ በርሱ ላይ ጀነትን እርም የሚያደርግ ቢሆን እንጂ።
አላህ አንድ ሀላፊነት ላይ ሹሞት የተሰጠውን ሀላፊነት የሚያታልል ሆኖ የሚሞት ባሪያ የለም አላህ በርሱ ላይ ጀነትን እርም የሚያደርግ ቢሆን እንጂ።
ከመዕቂል ቢን የሳር አልሙዘኒይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: እኔ የአላህን መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "አላህ አንድ ሀላፊነት ላይ ሹሞት የተሰጠውን ሀላፊነት የሚያታልል ሆኖ የሚሞት ባሪያ የለም አላህ በርሱ ላይ ጀነትን እርም የሚያደርግ ቢሆን እንጂ።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە සිංහල ไทย دری Fulfulde Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių or Română Kinyarwanda Српски O‘zbek Moore नेपाली Oromoo Wolof Soomaali Malagasy Български Українська Azərbaycan ქართული ln bm тоҷикӣالشرح
እያንዳንዱ አላህ በሰዎች ላይ ተጠያቂና ሀላፊ ያደረገው ሁሉ እንደመሪነት ጠቅላይ ሀላፊነትን የሚያስተዳድርም ይሁን ወይም በቤቱ ሀላፊ እንደሆነ ወንድና በቤቷ ሀላፊ እንደሆነች ሴት ውስን ሀላፊነትም ይሁን የሀላፊነት ግዴታውን ካጓደለ፣ ቅን ሳይሆን ካጭበረበረና ዲናዊና ዓለማዊ ግዴታውን ካጠፋ ለከባድ ቅጣት እንደተገባ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።فوائد الحديث
ይህ ዛቻ በጠቅላይ መሪውና ሚኒስትሮቹ ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን አላህ በሀላፊነት የሾመውን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው።
በአንዳች የሙስሊሞች ጉዳይ ላይ የተሾመ ሰው ያለበት ግዴታ ለነሱ ቅን መሆን፣ አደራውን በመወጣት ላይ መታገልና ማጭበርበርን መጠንቀቅ ነው።
ጠቅላይም ይሁን ውስን፣ ትልቅም ይሁን ትንሽ ሀላፊነት ላይ የተሾመ ሁሉ ተጠያቂነቱ ትልቅ መሆኑን እንረዳለን።
التصنيفات
ሸሪዓዊ ፖለቲካ