በቃል ኪዳን ስር ያለን (ሙዓሀድን) የገደለ ሰው የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታዋ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት በኃላ ነው።

በቃል ኪዳን ስር ያለን (ሙዓሀድን) የገደለ ሰው የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታዋ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት በኃላ ነው።

ከዐብደሏህ ቢን ዓምር (ረዲየሏሁ ዓንሁማ) አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ማለታቸው ተላልፏል፡ "በቃል ኪዳን ስር ያለን (ሙዓሀድን) የገደለ ሰው የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታዋ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት በኃላ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙዓሀድን በገደለ ሰው ላይ ያለበትን ከባድ ዛቻ ገለፁ። ሙዓሀድ ማለት ከከሀዲያን መካከል በቃል ኪዳንና በደህንነት ከለላ ወደ ኢስላም ሀገር የገባ ነው። እሱን የገደለ የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት ነው።

فوائد الحديث

ከከሀዲያን መካከል "ሙዓሀድን" ፣ "ዚሚይን" እና "ሙስተእመንን" መግደል ክልክልና ከትላልቅ ወንጀል የሚመደብም ነው።

"ሙዓሀድ" ማለት: ከከሀዲያን መካከል በሀገሩ እየኖረ ሙስሊሞችን ላይዋጋ እነሱም ላይዋጉት ከሙስሊሞች ጋር ቃል ኪዳን የተጋባ ነው።

"ዚሚይ" ማለት: በሙስሊሞች ሀገር እንደሀገሩ እየኖረ ግብር የሚከፍል ነው።

"ሙስተእመን" ማለት ደግሞ ለተወሰነ ወቅት በቃል ኪዳንና ደህንነት ከለላ ወደ ሙስሊሞች ሀገር የገባ ሰው ነው።

ከሙስሊሞች ውጪ ካሉ ጋር ቃል ኪዳንን ማፍረስ መከልከሉን እንረዳለን።

التصنيفات

የዚሚዮች (ግብር እየከፈሉ በሙስሊም ሀግር የሚኖሩ) ህግጋት