إعدادات العرض
የሙናፊቅ ምሳሌው በሁለት (የፍየል) መንጎች መካከል እንደዋለለች ፍየል ነው። አንድ ጊዜ ወደ አንዱ ሌላ ጊዜም ወደ ሌላኛው ትሄዳለች።
የሙናፊቅ ምሳሌው በሁለት (የፍየል) መንጎች መካከል እንደዋለለች ፍየል ነው። አንድ ጊዜ ወደ አንዱ ሌላ ጊዜም ወደ ሌላኛው ትሄዳለች።
ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "የሙናፊቅ ምሳሌው በሁለት (የፍየል) መንጎች መካከል እንደዋለለች ፍየል ነው። አንድ ጊዜ ወደ አንዱ ሌላ ጊዜም ወደ ሌላኛው ትሄዳለች።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Español Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe Bosanski සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa മലയാളം తెలుగు Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া Shqip دری Ελληνικά Български Fulfulde Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy or Română Kinyarwanda Српски тоҷикӣ O‘zbek नेपाली Moore Kurdî Oromoo Wolof Soomaali Français Tagalog Azərbaycan Українська bm தமிழ் Deutsch ქართული Português mk Magyarالشرح
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የሙናፊቅን ሁኔታ ከሁለት የፍየል መንጋ የትኛውን የፍየል መንጋ መከተል እንዳለባት እንዳላወቀች አንድ ፍየል አምሳያ እንደሆነ ገለፁ። ወደዛ መንጋ አንዴ ትሄዳለች ወደሌላኛው ደግሞ ሌላ ጊዜ ትሄዳለች። እነሱም በኢማንና ክህደት መካከል የዋለሉ ናቸው። በውጫዊና ውስጣዊ ማንነታቸው ከአማኞችም ጋር አይደሉም ከከሀዲዎችም ጋር አይደሉም። በተቃራኒ ውጫቸው ከአማኞች ጋር ሲሆን ውስጣቸው በጥርጣሬና ማወላወል የተሞላ ነው። ልባቸው አንዳንዴ ወደ አማኞች ሲዘነበል አንዳንዴ ደግሞ ወደከሀዲያን ይዘነበላል።فوائد الحديث
ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ቀና ጎዳና መሀል የተፈለገውን ሀሳብ በደንብ እንዲረዱት ምሳሌ መጥቀስ አንዱ ነው።
ሙናፊቆች ያለባቸውን የማወላወል፣ የጥርጣሬና አለመረጋጋት ባህሪ መገለፁ።
ከሙናፊቆች መገለጫ መጠንቀቅ እንዲሁም በውጫዊም ሆነ በውስጣዊ እምነታችን ቆራጥና እውነተኛ መሆን እንዳለብን መነሳሳቱ።
التصنيفات
ንፍቅና (ኒፋቅ)