إعدادات العرض
አንዳችሁ ዝንባሌው ይዤ የመጣሁትን እስከሚከተል ድረስ አላመነም።
አንዳችሁ ዝንባሌው ይዤ የመጣሁትን እስከሚከተል ድረስ አላመነም።
ከአቡ ሙሐመድ ዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዓስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "አንዳችሁ ዝንባሌው ይዤ የመጣሁትን እስከሚከተል ድረስ አላመነም።"
[قال النووي: حديث صحيح] [رويناه في كتاب الحجة بإسناد صحيح]
الترجمة
العربية Español English اردو Indonesia বাংলা Français Türkçe Русский Bosanski සිංහල हिन्दी 中文 فارسی Tiếng Việt Tagalog Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ ไทย Deutsch پښتو অসমীয়া Shqip Nederlands ગુજરાતી Кыргызча नेपाली Lietuvių دری Српски тоҷикӣ Kinyarwanda Magyar Čeština Moore Malagasy Oromoo ಕನ್ನಡ Wolof Azərbaycan O‘zbek Українська ქართული Македонски ភាសាខ្មែរ Bambara ਪੰਜਾਬੀ मराठी Kirundi Kurmancî Bahasa Melayuالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አንድ ሰው ውዴታው መልክተኛው -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ይዘውት የመጡትን ትእዛዛትን፣ ክልከላዎችንና ሌሎችንም እስከሚከተል ድረስ፤ እርሳቸው ያዘዙትን እስኪወድና የከለከሉትንም እስኪጠላ ድረስ ኢማኑ የተሟላ አማኝ አይሆንም ብለው አብራሩ።فوائد الحديث
ይህ ሐዲሥ ለሸሪዓ እጅ ለመስጠትና ታዛዥ ለመሆን መርህ የሆነ ሐዲሥ ነው።
የአይምሮውን ወይም የባህሉን ፍርድ መልክተኛው -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ይዘውት ከመጡት መመርያ የሚያስቀድም ሰው ከርሱ ላይ ኢማን ውድቅ መደረጉ ለሁሉም ሰው ማስጠንቀቂያ ነው።
ሐዲሡ ላይ «ይዤው ለመጣሁት» ማለታቸው በሁሉም ነገር ሸሪዓን ማስዳኘት ግዴታ መሆኑን ያስረዳናል።
ኢማን በአምልኮ ይጨምራል በወንጀል ደግሞ ይቀንሳል።
