አንዲትም አንቀጽ ቢሆን ከኔ አስተላልፉ። ከቤተ እስራኤላውያንም አውሩ ችግር የለውም። ሆን ብሎ በኔ ላይ የዋሸ ከእሳት የሆነን መቀመጫውን ያመቻች።

አንዲትም አንቀጽ ቢሆን ከኔ አስተላልፉ። ከቤተ እስራኤላውያንም አውሩ ችግር የለውም። ሆን ብሎ በኔ ላይ የዋሸ ከእሳት የሆነን መቀመጫውን ያመቻች።

ከዐብደሏህ ቢን ዐምር ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "አንዲትም አንቀጽ ቢሆን ከኔ አስተላልፉ። ከቤተ እስራኤላውያንም አውሩ ችግር የለውም። ሆን ብሎ በኔ ላይ የዋሸ ከእሳት የሆነን መቀመጫውን ያመቻች።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከርሳቸው የተማርነውን ቁርአናዊም ይሁን ሐዲሣዊ እውቀት አንድ አንቀፅ ያህል ትንሽ እንኳ ቢሆን እንድናስተላልፈው አዘዙን፤ ይህም ግን የምንጣራበትንና የምናደርሰውን መልእክት ተረድተነው መሆኑ ቅድመ መስፈርቱ ነው። ከዚያም ሽሪዓችን ጋር እስካልተጋጨ ድረስ ከበኒ ኢስራኢሎች የተከሰተባቸውን ክስተትና መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ ማውራታችንም ችግር እንደሌለው ገለፁ። ከዚያም በሳቸው ላይ ከመቅጠፍ አስጠነቀቁ፤ ሆን ብሎ በሳቸው ላይ የዋሸም ጀሀነም ውስጥ ማረፊያውን እንዲይዝ አሳሰቡ።

فوائد الحديث

የአላህን ሸሪዓ ማስተላለፍ እንደሚበረታታና ማንኛውም ሰው የሸመደደውና የተረዳውን ትንሽም ቢሆን ማድረስ እንዳለበት እንረዳለን።

አሏህን በትክክል ለማምለክና መልዕክቱንም ለማድረስ እንዲያስችል ሸሪዓዊ እውቀትን መፈለግ ግዴታ ነው።

ይህ ከባድ ዛቻ ከሚመለከታቸው ሰዎች ላለመሆን ሲባል የትኛውንም ሐዲሥ ከማስተላለፋችንና ከማሰራጨታችን በፊት በትክክል ከሳቸው መሆኑን ማረጋገጥ ግዴታ ነው።

ውሸት ላይ ላለመውደቅ ሲባል በተለይም በአሏህ ሸሪዓ ላይ በንግግራችን እውነተኞችና የምናወራውም የተሟላ መረጃ ያለንን ጉዳይ መሆኑ እንደሚበረታታ እንረዳለን።

التصنيفات

የሱና አንገብጋቢነትና ያለው ደረጃ, ወደ አላህ የመጣራት ፍርድ