የዐስርን ሶላት የተወ ሰው በርግጥም ስራው ተበላሸ።'

የዐስርን ሶላት የተወ ሰው በርግጥም ስራው ተበላሸ።'

ከቡረይዳህ ቢን ሑሰይብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "የዐስርን ሰላት ወቅቱ እንደገባ ቶሎ ስገዱ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋልና: ' የዐስርን ሶላት የተወ ሰው በርግጥም ስራው ተበላሸ።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዐስርን ሶላት ሆን ብሎ ወቅቱን ከማዘግየት አስጠነቀቁ። ይህንን የፈፀመ ሰው ስራው ተበላሽቶ ከንቱ ይቀራል።

فوائد الحديث

የዐስርን ሶላት በመጀመሪያ ወቅቱ በመጠባበቅ ላይና ወደዚህ ተግባር በመቻኮል ላይ መነሳሳቱ፤

የዐስርን ሶላት የተወ ሰው ላይ ብርቱ ዛቻ መምጣቱንና ዐስርን ከወቅቱ ማሳለፍ ሌሎችን ሶላቶች ከወቅቱ ከማሳለፍ የበለጠ እጅግ ከባድ መሆኑን እንረዳለን። የዐስር ሶላት {በሶላቶች (በተለይ) በመካከለኛይቱም ሶላት ላይ ተጠባበቁ፡፡} [አልበቀራህ: 238] በሚለው የአላህ ንግግር ላይ ባለው ትእዛዝ ልዩ ሆና የተወሳች ምርጧ ሶላት ናትና።

التصنيفات

የሶላት ግዴታነትና የተወው ሰው ፍርድ, የሶላት ግዴታነትና የተወው ሰው ፍርድ