إعدادات العرض
ጻፍ! ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ከዚህ አንደበት እውነት እንጂ አይወጣም።'
ጻፍ! ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ከዚህ አንደበት እውነት እንጂ አይወጣም።'
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የምሰማውን ነገር ሁሉ መጠበቅ ፈልጌ እፅፈው ነበር። ቁረይሾች እንዲህ በማለት ከለከሉኝ 'ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የምትሰማውን ነገር ሁሉ ትፅፋለህን? የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኮ ሰው ናቸው በቁጣና በደስታ ሰአትም ይናገራሉ!' ከመፃፍ ተቆጥቤ ይህንን ለአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አወሳሁ። እሳቸውም በጣታቸው ወደ አፋቸው እየጠቆሙ እንዲህ አሉኝ: ' ጻፍ! ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ከዚህ አንደበት እውነት እንጂ አይወጣም።'"
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa తెలుగు Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली മലയാളം Bosanski Italiano ಕನ್ನಡ Kurdî Oromoo Română Shqip Soomaali Српски Українська Wolof Moore Tagalog Malagasy O‘zbek தமிழ்الشرح
ዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ አሉ: ሁሉንም ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የምሰማውን ነገር በጽሑፍ መጠበቅ ፈልጌ እጽፈው ነበር። ከቁረይሽ የሆኑ ሰዎችም እንዲህ በማለት ከለከሉኝ "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰው ናቸው በቁጣና በደስታ ሰአትም ይናገራሉ፤ ሊሳሳቱም ይችላሉ።" እኔም ከመጻፍ ተቆጠብኩኝ። እነርሱ የተናገሩትን ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነገርኳቸው። በጣታቸው ወደ አፋቸው እየጠቆሙ እንዲህ አሉኝ: "ጻፍ! ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! በደስታም ይሁን በንዴት በማንኛውም ሁኔታ ላይ ብሆን ከዚህ አንደበት እውነት እንጂ አይወጣም።" በርግጥ ከፍ ያለው አላህም ስለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብሏል፦ {ከልብ ወለድም አይናገርም።* እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጂ ሌላ አይደለም።} [አንነጅም:3 -4]فوائد الحديث
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በደስታም ይሁን በንዴት ወቅት ከጌታቸው በሚያደርሱት ነገር ፍፁም ናቸው።
ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ሱናን በመጠበቅና በማስተላለፍ ላይ ያላቸውን ጉጉት እንረዳለን።
አስፈላጊ ከሆነ ጉዳዩን አፅንኦት ለመስጠት ያህል መሀላ ሳንጠየቅም መማል እንደሚፈቀድ።
እውቀትን በጽሑፍ ማስቀመጥ እውቀትን ከሚጠብቁ ዘዴዎች መካከል ዋነኛው መሆኑን እንረዳለን።