‹ከሚሰርቁ ሰዎች ሁሉ እጅግ መጥፎው ሶላቱን የሚሰርቅ ነው።› እርሱም ‹እንዴት ሶላቱን ይሰርቃታል?› አላቸው። እርሳቸውም ‹ሩኩዑንም ሆነ ሱጁዱን ባለማሟላት።› ብለው መለሱለት።

‹ከሚሰርቁ ሰዎች ሁሉ እጅግ መጥፎው ሶላቱን የሚሰርቅ ነው።› እርሱም ‹እንዴት ሶላቱን ይሰርቃታል?› አላቸው። እርሳቸውም ‹ሩኩዑንም ሆነ ሱጁዱን ባለማሟላት።› ብለው መለሱለት።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹ከሚሰርቁ ሰዎች ሁሉ እጅግ መጥፎው ሶላቱን የሚሰርቅ ነው።› እርሱም ‹እንዴት ሶላቱን ይሰርቃታል?› አላቸው። እርሳቸውም ‹ሩኩዑንም ሆነ ሱጁዱን ባለማሟላት።› ብለው መለሱለት።"

[ሶሒሕ ነው።] [ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በስርቆት እጅግ በጣም መጥፎ ሰው ከሶላቱ የሚሰርቅ ሰው መሆኑን ገለፁ። ይህም ከዚህ ሌባ ተቃራኒ የሌላን ሰው ገንዘብ የወሰደ በዚህች አለም ሊጠቀምበትም ይችል ይሆናል። ይህ ሌባ ግን ከራሱ የምንዳና አጅር ሐቅ የሚሰርቅ ነው። ሶሐቦችም "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እንዴት አንድ ሰው ከሶላቱ ይሰርቃል?" ብለው ጠየቁ። እርሳቸውም "ሩኩዑንም ሆነ ሱጁዱን አያሟላም።" ብለው መለሱ። ይህም በሩኩዑም በሱጁዱም ሲጣደፍ በተሟላ መልኩ እነርሱን አለመፈፀሙ ነው።

فوائد الحديث

ሶላትን ማሳመር፣ ማእዘናቶቿንም በእርጋታና በተመስጦ መፈፀም አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።

ሩኩዑም ሱጁዱም የማያሟላ ሰው ከዚህ ተግባሩ ለማራቅና ክልክልነቱን ለማስገንዘብ ሲባል በሌባነት መገለፁን፤

ሶላት ውስጥ ሩኩዕና ሱጁድን መሙላትና እነርሱንም ቀጥ ብሎ መፈፀሙ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

የሰላት ማዕዘናት, የሶላት አሰጋገድ, የሰጋጆች ስህተት