إعدادات العرض
ራስን መጉዳትም ሆነ ሌላውን መጉዳት የለም።
ራስን መጉዳትም ሆነ ሌላውን መጉዳት የለም።
ከአቡ ሰዒድ ሰዕድ ቢን ማሊክ ቢን ሲናን አልኹድሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "ራስን መጉዳትም ሆነ ሌላውን መጉዳት የለም።"
[ሐሰን ነው።] [رواه ابن ماجه والدارقطني وغيرهما مسندًا]
الترجمة
العربية Español English اردو Indonesia বাংলা Français Türkçe Русский Bosanski සිංහල हिन्दी 中文 فارسی Tiếng Việt Tagalog Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ ไทย Deutsch پښتو অসমীয়া Shqip Nederlands ગુજરાતી Кыргызча नेपाली Lietuvių دری Српски тоҷикӣ Kinyarwanda Magyar Čeština Moore Malagasy Oromoo ಕನ್ನಡ Wolof Azərbaycan O‘zbek Українська ქართული Македонски ភាសាខ្មែរ Bambara ਪੰਜਾਬੀ मराठी Kirundi Kurmancî Bahasa Melayuالشرح
ነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጉዳትን በማንኛውም አይነት መገለጫው ከነፍስ ላይም ይሁን ከሌሎች ላይ መከላከል ግዴታ እንደሆነ ገለፁ። ስለሆነም አንድ ሰው ራሱንም ይሁን በተመሳሳይ መልኩ ሌላንም ቢሆን ማወክ አይፈቀድለትም። እንዲሁም ጉዳትን በጉዳት መመለስም አይፈቀድለትም። ምክንያቱም ወሰን ባልታለፈበት የማመሳሰል (የቂሷስ ህግ) ካልሆነ በስተቀር ጉዳት በመጉዳት አይወገድምና።فوائد الحديث
ከማመሳሰል (ከደረሰበት በደል) በበዛ መልኩ መበቀል መከልከሉን እንረዳለን።
አላህ ባሮቹን በአንዳችም የሚጎዳቸው በሆነ ነገር አላዘዛቸውም።
ይህ ሐዲሥ በንግግርም ይሁን በተግባር ወይም በመተውም ቢሆን መጉዳትና መበቀል ክልክል ለመሆኑ መርህ የሆነ ሐዲሥ ነው።
ከሸሪዐ መርሆዎች መካከል አንዱ: - "ጉዳት መወገድ ይገባዋል።" የሚል ነው። ሸሪዓ በፍፁም ጉዳትን እንደማያፀናና መጉዳትን እንደሚያወግዝ እንረዳለን።
