ውሸት መሆኑን እያወቀ ከኔ አንድ ሐዲሥን ያወራ ሰው ከውሸታሞች አንዱ ነው።

ውሸት መሆኑን እያወቀ ከኔ አንድ ሐዲሥን ያወራ ሰው ከውሸታሞች አንዱ ነው።

ከሰሙራ ቢን ጁንዱብና ሙጚራ ቢን ሹዕባ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ውሸት መሆኑን እያወቀ ከኔ አንድ ሐዲሥን ያወራ ሰው ከውሸታሞች አንዱ ነው።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በርሳቸው ላይ እየዋሸ እንደሆነ እያወቀ ወይም እየተጠራጠረ ወይም በአብዛኛው ግምቱ እየዋሸ እንደሆነ እየተሰማው ከርሳቸው ንግግርን ያስተላለፈና ያወራ ሰው ይህንን ውሸት ለመጀመሪያ ጊዜ ከቀጠፈው ጋር (በወንጀሉ) ይጋራል።

فوائد الحديث

ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተወሩን ሐዲሦች ማረጋገጥና ከማውራት በፊት ትክክለኝነቱን ማረጋገጥ እንደሚገባ እንረዳለን።

የውሸታምነት ባህሪ ውሸትን በፈጠረ ሁሉ ላይ፣ በማስተላለፉ በተሳተፈ ላይና በሰዎች መካከል ያሰራጨውም ሁሉ ይገለፅበታል።

የተፈበረከ ሐዲሥ መሆኑን ባወቀ ሰው ወይም የተፈበረከ መሆኑን ጥርጣሬው ባመዘነ ሰው ላይ ለማስጠንቀቅ ካልሆነ በቀር የተፈበረከ ሐዲሥን ማውራት አይፈቀድም።

التصنيفات

የሱና አንገብጋቢነትና ያለው ደረጃ, ውግዝ ስነ-ምግባር