መፀዳጃ ቦታ የመጣችሁ ጊዜ ወደ ቂብላ አትዙሩም ጀርባ አትስጡም! ነገር ግን ወደ ምስራቅ ወይም ምዕራብ ዙሩ

መፀዳጃ ቦታ የመጣችሁ ጊዜ ወደ ቂብላ አትዙሩም ጀርባ አትስጡም! ነገር ግን ወደ ምስራቅ ወይም ምዕራብ ዙሩ

ከአቡ አዩብ አልአንሷሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "መፀዳጃ ቦታ የመጣችሁ ጊዜ ወደ ቂብላ አትዙሩም ጀርባ አትስጡም! ነገር ግን ወደ ምስራቅ ወይም ምዕራብ ዙሩ" አቡ አዩብ እንዲህ አለ "ሻም ስንገባ ወደ ቂብላ አቅጣጫ የተገነባ መፀዳጃ ቤት አገኘን። ትንሽ ዘንበል እያልን እየተፀዳዳን አላህንም ምህረት እንጠይቀዋለን።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሽንትም ይሁን ለሰገራ መፀዳዳት የፈለገ ሰው ወደ ካዕባ አቅጣጫ ዞሮም ይሁን ለካዕባ ጀርባን ሰጥቶ መፀዳዳቱን ከለከሉ። ቂብላው እንደ መዲና ነዋሪዎች ከሆነ ማድረግ ያለበት ወደ ምስራቅ ወይም ምዕራብ አቅጣጫ ዘንበል ማለት ነው። ቀጥሎ አቡ አዩብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ወደ ሻም የገቡ ጊዜ ወደ ካዕባ አቅጣጫ የተገነባ ለመፀዳጃነት የተዘጋጀ መፀዳጃ ቤት እንዳገኙ፤ በአካላቸውም ከቂብላ ዘንበል እንደሚሉና ከዚህም ጋር ግን አላህን ምህረት እንደሚጠይቁ ተናገረ።

فوائد الحديث

በዚህ ድንጋጌ የተፈለገው ጥበብ የላቀውን ካዕባ ማላቅና ማክበር ነው።

ከመፀዳጃ ስፍራ ከወጣን በኋላ ኢስቲግፋር ማድረግ እንደሚገባ እንረዳለን።

የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የማስተማር ዘዴ ማማሩን እንረዳለን። ይህም ክልክሉን ከጠቀሱ በኋላ የሚፈቀደውን በመጠቆማቸው ነው።

التصنيفات

ነጃሳን ማስወገድ, የመፀዳጃ ቤት ስነ-ስርዓት