(ጎረቤቴን) ያስወርሰዋል ብዬ እስከማስብ ድረስ ጂብሪል በጎረቤት (ሐቅ ዙሪያ) እኔን ከማዘዝ አልተወገደም።

(ጎረቤቴን) ያስወርሰዋል ብዬ እስከማስብ ድረስ ጂብሪል በጎረቤት (ሐቅ ዙሪያ) እኔን ከማዘዝ አልተወገደም።

ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "(ጎረቤቴን) ያስወርሰዋል ብዬ እስከማስብ ድረስ ጂብሪል በጎረቤት (ሐቅ ዙሪያ) እኔን ከማዘዝ አልተወገደም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጂብሪል ለጎረቤታቸው ትኩረት እንዲቸሩ፣ ሐቁን እንዲጠብቁ፣ እንዳያውኩት፣ ለርሱ በጎ እንዲውሉ፣ በሚያደርስባቸው ጉዳት እንዲታገሱ ከማዘዝና ከመደጋገም እንዳልተወገደ ተናገሩ። ይህም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጎረቤት ሀቅ ክብደትና ጂብሪል ይህን ትእዛዝ ከመደጋገሙ የተነሳ ከሞቱ በኋላ ትተውት የሚያልፉትን ገንዘባቸውን ለጎረቤታቸው እንዲሰጡ የሚያዝ ወሕይ ሊወርድ ይሆን ብለው እስኪያስቡ ደረሱ። ጎረቤት ሲባልም ሙስሊምም ሆነ ካፊር፣ ዘመድም ሆነ ባዳ ማንኛውም ለቤት ቅርብ የሆነ ማለት ነው።

فوائد الحديث

የጎረቤት ሐቅ ክብደትንና ይህንን መጠባበቅ ግዴታ እንደሆነ ፤

የጎረቤት ሐቅ በአደራ መልክ መጠንከሩ ጎረቤትን ማክበርን፣ መውደድን፣ ለርሱ በጎ መዋልን፣ ከርሱ ጉዳትን መከላከልን፣ ሲታመም መጠየቅን፣ በደስታ ወቅት ማስደሰትን፣ በመከራ ወቅት ማፅናናትን ያስፈርዳል ፤

የጎረቤት ደጃፍ በቀረበ ልክ ሐቁም የጠነከረ ይሆናል።

ሸሪዓ ለጎረቤት በጎ መዋልና ከነሱ ላይ ጉዳትን መከላከልን የመሰለ ለማህበረሰቡ ጥቅም ያላቸው ድንጋጌዎችን ይዞ በመምጣቱ ረገድ የተሟላ መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

ስምምነትና የጉርብትና ህግጋት