አውቆ መጉዳትም ሆነ ሳያውቁ መጎዳዳትም የለም (አይቻልም)። ጎጂን አላህ ይጎዳዋል። ሰዎችን ያስጨነቀ አላህ ያጨናንቀዋል።

አውቆ መጉዳትም ሆነ ሳያውቁ መጎዳዳትም የለም (አይቻልም)። ጎጂን አላህ ይጎዳዋል። ሰዎችን ያስጨነቀ አላህ ያጨናንቀዋል።

ከአቢ ሰዒድ አልኹድሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "አውቆ መጉዳትም ሆነ ሳያውቁ መጎዳዳትም የለም (አይቻልም)። ጎጂን አላህ ይጎዳዋል። ሰዎችን ያስጨነቀ አላህ ያጨናንቀዋል።"

[በማመሳከሪያዎቹ ሶሒሕ ነው።] [ዳረቁጥኒይ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጉዳትን በማንኛውም አይነት መገለጫው ይሁን ከነፍስ ላይም ይሁን ከሌሎች ላይ መከላከል ግዴታ እንደሆነ ገለፁ። ስለሆነም አንድም ሰው ራሱንም ይሁን በተመሳሳይ መልኩ ሌላንም ቢሆን ማወክ አይፈቀድለትም። እንዲሁም ጉዳትን በጉዳት መመለስም አይፈቀድለትም። ምክንያቱም ወሰን ባልታለፈበት የማመሳሰል (የቂሷስ ህግ) ካልሆነ በስተቀር ጉዳትን በመጉዳት አይወገድምና። ከዚያም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰዎችን ለሚጎዳ ሰው ጉዳት እንደሚያገኘው ፤ ሰዎችን ለሚያጨናንቅም መጨናነቅ እንደሚያገኘው ዛቱ።

فوائد الحديث

ከማመሳሰል (ከደረሰበት በደል) በበዛ መልኩ መበቀል መከልከሉን፤

አላህ ባሮቹን በአንዳችም የሚጎዳቸው በሆነ ነገር አላዘዛቸውም ፤

በንግግር ወይም በተግባር ወይም በመተውም ቢሆን አውቆም ይሁን ሳያውቁ መጉዳት መከልከሉ ፤

ምንዳ በስራው አይነት ነው የሚሰጠው። የጎዳ ሰው አላህ ይጎዳዋል ፤ ያስጨነቀም አላህ ያጨናንቀዋል።

ከሸሪዐ መርሆዎች መካከል አንዱ: - "ጉዳት መወገድ ይገባዋል።" የሚል ነው። ሸሪዓ በፍፁም ጉዳትን እንደማያፀናና መጉዳትን እንደሚያወግዝ እንረዳለን።

التصنيفات

ፊቂሀዊ መርሆዎችና መሰረቶች