የሶላትን ጥሪ ትሰማለህን?' አሉት። እርሱም 'አዎን' አላቸው። እሳቸውም 'እንግዲያውስ ለጥሪው መልስ ስጥ!' አሉት።

የሶላትን ጥሪ ትሰማለህን?' አሉት። እርሱም 'አዎን' አላቸው። እሳቸውም 'እንግዲያውስ ለጥሪው መልስ ስጥ!' አሉት።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ አንድ ማየት የተሳነው ሰውዬ መጣ። 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ወደ መስጂድ የሚመራኝ መሪ የለኝም።' በማለት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በቤቱ መስገድን እንዲያገሩለት ጠየቀ። ለርሱም አግራሩለት። ለመሄድ የዞረ ጊዜ ጠሩትና 'የሶላትን ጥሪ ትሰማለህን?' አሉት። እርሱም 'አዎን' አላቸው። እሳቸውም 'እንግዲያውስ ለጥሪው መልስ ስጥ!' አሉት።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

አንድ አይነ ስውር ሰውዬ ወደ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመምጣት "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ዘንድ ለአምስቱ ሶላቶች እጄን ይዞ ወደ መስጂድ የሚወስደኝና የሚያግዘኝ የለም።" አለ። ፍላጎቱ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጀማዓን በመተው ለርሱ እንዲያግራሩለት ነው። ለርሱም አግራሩለት። ለመሄድ የዞረ ጊዜም ጠሩትና "የሶላትን አዛን ትሰማለህን?" አሉት። እርሱም "አዎን" አለ። እሳቸውም "የሶላቱን ተጣሪ ጥሪ መልስ" አሉት።

فوائد الحديث

ግዴታ ለሆነ ነገር ካለሆነ በቀር ማግራራት ስለማይኖር የጀማዓ ሶላት ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።

"ጥሪውን መልስ!" ከሚለው ቃላቸው አዛን የሚሰማ ሰው ላይ የጀማዓ ሶላት ግዴታ መሆኑን ይጠቁማል። ትእዛዝ በመሰረቱ የሚያስፈርደው ግዴታን ነውና።

التصنيفات

የጀማዓህ ሶላት ትሩፋትና ህግጋት