አላህ ሆይ! ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና እነርሱን ለችግር የዳረገ እርሱንም የሚቸገር አድርገው ። ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና ለነሱ የራራን ለርሱም ራራለት።

አላህ ሆይ! ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና እነርሱን ለችግር የዳረገ እርሱንም የሚቸገር አድርገው ። ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና ለነሱ የራራን ለርሱም ራራለት።

ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: የአላህ መልክተኛን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤቴ ውስጥ ይህንን ሲሉ ሰምቻለሁ: "አላህ ሆይ! ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና እነርሱን ለችግር የዳረገ እርሱንም የሚቸገር አድርገው ። ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና ለነሱ የራራን ለርሱም ራራለት።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የሙስሊሞች ጉዳዮች ውስጥ በየትኛውም ትንሽም ይሁን ትልቅ ሹመት ፣ አጠቃላይም ይሁን ቁንፅል ሹመትን የተሾመ ከዚያም ለሙስሊሞች ሳይራራ ችግርን በነርሱ ላይ የሚያባብስባቸው የሆነን ሰው ሁሉ ላይ አላህ በሰራው ስራ ተመሳሳይ እሱንም ለችግር እንዲዳርገው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዱዓእ አደረጉበት። ለነርሱ የራራና ጉዳዮቻቸውን ባቀለለ ላይም አላህ ለርሱ እንዲራራና ጉዳዮቹን እንዲያገራለት ዱዓ አደረጉለት።

فوائد الحديث

ከሙስሊሞች ጉዳዮች መካከል አንድ ነገር ላይ የተሾመ ሰው በቻለው መጠን ለነርሱ መራራት ግዴታው መሆኑን ፤

ምንዳ የሚሰጠን በስራችን አይነት መሆኑን፤

የመራራትና የሀይለኝነት መለኪያ ሚዛኑ ቁርአንና ሐዲሥና ባልተፃረረ መልኩ መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

የመሪነት መስፈርቶች, የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ርህራሄ