إعدادات العرض
የቤተሰብ ፊቂህ
የቤተሰብ ፊቂህ
2- 'ከአማኞች መካከል ኢማናቸው የተሟላው ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ የሆኑት ናቸው ፤ ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ምርጥ የሆኑት ናቸው።'
3- ዱንያ መጣቀሚያ ናት። ከዱንያ መጣቀሚያዎች ምርጡ መልካም ሚስት ናት።
4- አላህ እንዲህ ብሏል 'የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ላንተም ይሰጥሃል!'
5- 'ልታሟሉት ከሚገቡ መስፈርቶች ሁሉ ልታሟሉት እጅግ የተገባው ብልትን ሐላል ያደረጋቹበትን መስፈርት ነው።'
6- ሰውዬው (ምንዳ እንደሚያገኝበት) እያሰበ ለቤተሰቡ ወጪ ያወጣ ጊዜ ለርሱ ምፅዋት ትሆንለታለች።
7- የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፀጉርን አንዱን ተላጭቶ አንዱን ትቶ ከመቆረጥ ከልክለዋል።
8- የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ የጉዳይ ጊዜ ኹጥባን (ኹጥበቱል ሓጃህ) አስተማሩን
10- ዱንያ ጣፋጭና አረንጓዴ (ለምለም) ናት። አላህም እንዴት እንደምትሰሩ ሊያያችሁ በውስጧ ምትኮች አድርጓችኋል። ዱንያንም ተጠንቀቁ! ሴቶችንም ተጠንቀቁ!
11- አንድ አማኝ ወንድ አንዲትን አማኝ እንስት አይጥላ። ከርሷ አንድ ባህሪዋን ቢጠላ እንኳ ሌላ የሚወደው ባህሪ አላትና።
12- ሁላችሁም እረኞች (ሀላፊ) ናችሁ። ስለምትጠብቁት ነገርም ትጠየቃላችሁ።
16- 'ሴት ልጅ ከርሷ ጋር ባሏ ወይም ዘመዷ ከሌሉ በቀር ሁለት ቀን የሚያስኬድ መንገድን አትጓዝ።
22- እነዚህ ሁለቱ ከኡመቴ በወንዶቹ ላይ ክልክል ናቸው። ለሴቶቹ ግን የተፈቀደ ነው።