إعدادات العرض
ንፅህና (ጦሀራ)
ንፅህና (ጦሀራ)
2- ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለውን ፂም) አሳጥሩ ሪዛችሁን (የመንጋጭላ ፂማችሁን) ልቀቁ!
3- እኔ እንዳደረጉት አይነት ዉዱእ አድርጎ ከዚያም ነፍሱን ምንም በሃሳብ ሳያደፈርስ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው ያሳለፈው ወንጀሉ ተምሮለታል።' አሉ።'
4- አንዳችሁ ዉዱእ በሌለው ጊዜ ዉዱእ እስኪያደርግ ድረስ አላህ ሶላቱን አይቀበለውም።
5- 'ሲዋክ አፍን የሚያጠራ (የሚያፀዳ)፤ የአሏህንም ውዴታ የሚያስገኝ ነው።'
6- ውዱእን አሳምሮ ያደረገ ወንጀሎቹ ከጥፍሮቹ ስር ሳይቀር ከሰውነቱ ባጠቃላይ ይወጣሉ።'
9- እኔ ንፁህ እንደሆነ ነው ያደረግኳቸውና ተዋቸው።
10- ይህ የደም ስር መቆረጥ ነው። ባይሆን የወር አበባ ስታይበት በነበርሽው የቀናት ልክ ሶላትን ተይ! ከዚያም ታጠቢና ስገጂ።' አሏት።
11- አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው።
13- መፀዳጃ ቦታ የመጣችሁ ጊዜ ወደ ቂብላ አትዙሩም ጀርባ አትስጡም! ነገር ግን ወደ ምስራቅ ወይም ምዕራብ ዙሩ
17- ከጀናባ አስተጣጠብ ሁኔታ
20- የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ አደረጉላቸው።
32- አንዳችሁ ዉዱእ አድርጎ ኹፎቹን የለበሰ እንደሆነ እነርሱን እንደለበሰ ይስገድ። በነርሱም ላይ ያብስና ከዚያም ለጀናባ ካልሆነ በቀር ከፈለገ አያውልቃቸው።
33- ከፀዳን በኋላ የሚወጣንን ድፍርስና ዳለቻ ቀለም ፈሳሽ እንደ ምንም ነገር አንቆጥረውም ነበር።
34- 'የወር አበባሽ የሚያግድሽ ቀናት ያክል (ሳትሰግጂ ሳትፆሚ) ቆዪ ከዚያም ታጠቢ።'
35- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ሶላት ወቅት ዉዱእ ያደርጉ ነበር።
36- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ አንድ ጊዜ ዉዱእ አደርገዋል።
37- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለት ሁለት ጊዜ ዉዱእ አድርገዋል።
39- እያንዳንዱ ሙስሊም በየሰባት ቀኑ አንድ ጊዜ ገላውን መታጠብ አለበት። ሲታጠብም ጭንቅላቱንም ገላውንም መታጠብ አለበት።
40- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ እስልምናን መቀበል ፈልጌ መጣሁ። እሳቸውም በውሃና በቁርቁራ ቅጠል እንድታጠብ አዘዙኝ።
41- ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ነበርኩ። ወደ ቆሻሻ መጣያ ዘንድ ሲደርሱ ቆመው ሸኑ።