إعدادات العرض
ሸሪዓዊ ስነ-ስረዓቶች
ሸሪዓዊ ስነ-ስረዓቶች
1- አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።
3- ሀሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አሉ። እሳቸውም "ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው።
4- ሲገናኙ ይህም እየዞረ ያኛውም እየዞረ ወንድሙን ከሶስት ሌሊቶች በላይ ሊያኮርፈው አይፈቀድለትም። ከሁለቱ ምርጡ በሰላምታ የሚጀምረው ነው።
5- ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሽቶን አይመልሱም ነበር።
6- 'አላህ ባሪያው ምግብን በልቶ እንዲያመሰግነው ወይም መጠጥን ጠጥቶ እንዲያመሰግነው ይወዳል።'
7- አንተ ልጅ ሆይ! ቢስሚላህ በል! በቀኝህ ብላ፣ ፊትህ ካለውም ብላ!
8- አንዳችሁ የበላ ጊዜ በቀኙ ይብላ። የጠጣም ጊዜ በቀኙ ይጠጣ። ሰይጣን የሚበላውም በግራው፤ የሚጠጣውም በግራው ነውና።
11- እኔ ንፁህ እንደሆነ ነው ያደረግኳቸውና ተዋቸው።
12- አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው።
13- አንዳችሁ እየሸና ሳለ ብልቱን በቀኝ እጁ አይያዘው፤ ሲፀዳዳም በቀኝ እጁ አይጥረግ፤ በእቃ ውስጥም አይተንፍስ!
21- የሚጋልብ ሰው በእግረኛ ላይ ሰላምታን ያቅርብ፤ እግረኛ በተቀማጭ ላይ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች በብዙ ሰዎች ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።'
23- የትንሳኤ ቀን ከመልካም ስነ ምግባር የበለጠ የአማኝን ሚዛን የሚደፋ አንድም ነገር የለም። አላህ ፀያፍ የሚሰራንና ፀያፍ የሚናገርን ይጠላል።
27- ወንድ ልጅ ወደ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ አይመልከት! ሴት ልጅም ወደ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ አትመልከት!
28- ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው፤ ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።
29- ቁርኣንን ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያነብ ምፅዋትን በይፋ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው፤ ቁርኣንን በዝግታ የሚያነብ ምፅዋትን በድብቅ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው።