إعدادات العرض
የዱዓና አዝካር ፊቅህ
የዱዓና አዝካር ፊቅህ
1- በላጩ ዚክር 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን በላጩ ዱዓእ ደግሞ 'አልሐምዱሊላህ' ማለት ነው።'
2- አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ ነው። (ስለዚህም) ዱዓእን አብዙ!
4- ለምላስ ቀላል የሆኑ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አርራህማን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላቶች አሉ
6- ''ሱብሓነሏህ ወልሐምዱሊላህ ወላኢላሃ ኢለሏህ ወሏሁ አክበር' ማለቴ ፀሀይ የወጣችበት ክልል ሁሉ (ከሚሰጠኝ) የበለጠ ወደእኔ እጅግ ተወዳጅ ነው።'
7- በምሽት ውስጥ የመጨረሻዎቹን የበቀራህ ምእራፍ ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው ይበቁታል።
9- አንድ ሰው ወደ ቤቱ ሲገባ በሚገባበት ወቅትም በሚበላበት ወቅትም አላህን ካወሳ ሰይጣን (ለባልደረቦቹ) 'ማደሪያም እራትም የላችሁም።' ይላል።
11- ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው በመጨረሻው የሌሊቱ አጋማሽ ነው።
12- እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ መልካም ነው። ከመልካም በቀርም አይቀበልም። አላህ መልክተኞችን ባዘዘው ነገር አማኞችንም አዟል።
15- አልላሁመ አስሊሕ ሊ ዲኒለዚ ሁወ ዒስመቱ አምሪ
16- አላህ ሆይ! በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤
21- 'ሱረቱል ኢኽላስ እና ሁለቱን መጠበቂያዎች (ሱረቱል ፈለቅና ሱረቱን-ናስን) ስታመሽና ስታነጋ ሶስት ጊዜ ካልክ ለሁሉም ነገር ይበቁሃል።' አሉኝ።
25- ይሄ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ስሜት የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ! ወደ ግራህም ሶስት ጊዜ ትፋ!