إعدادات العرض
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች - الصفحة 3
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች - الصفحة 3
4- ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ነበርኩ። ወደ ቆሻሻ መጣያ ዘንድ ሲደርሱ ቆመው ሸኑ።
15- አንዳችሁ ሰዎች ሰጡትም ከለከሉት ሰዎችን ከሚለምን ይልቅ ገመዱን ይዞ በጀርባው እንጨት አስሮ እያመጣ በመሸጥ አላህ ፊቱን (ከመገረፍ) ቢጠብቅለት የተሻለ ነው።
17- እነዚህ ሁለቱ ከኡመቴ በወንዶቹ ላይ ክልክል ናቸው። ለሴቶቹ ግን የተፈቀደ ነው።
18- አላህና መልክተኛው አስካሪ መጠጥን፣ በክትን፣ አሳማንና ጣዖታትን ከመሸጥ ከልክለዋል።
37- ከሁሉም የክራንቻ ጥርስ ባለቤት አውሬና ከሁሉም ባለጥፍር በራሪ ስጋ (መብላትን) ከልክለዋል።
38- በየሁሉም ሁለት አዛኖች መካከል ሶላት አለ። በየሁሉም ሁለት አዛኖች መካከል ሶላት አለ።" ቀጥለው በሶስተኛው "ለፈለገ ሰው" አሉ።
47- መሳሪያውን በኛ ላይ ያነሳ ከኛ አይደለም።
51- እኔ የማትጎዳና የማትጠቅም ድንጋይ መሆንህን አውቃለሁ። እኔ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሲስሙህ ባላይህ ኖሮ አልስምህም ነበር።
56- በአላህ መንገድ ላይ አንድ ቀን የጾመ ሰው አላህ ፊቱን ከእሳት ሰባ ዓመታት ያርቀዋል።
57- ሰዎች ማፍጠርን እስካቻኮሉ ድረስ መልካም ላይ ከመሆን አይወገዱም።
61- ሰሑር ተመገቡ! በሰሑር ውስጥ በረከት አለ።
62- ከረመዷን አንድ ቀንም ሆነ ሁለት ቀን በፊት ቀድማቹህ አትፁሙ። ነገር ግን ያስለመደው ጾም የነበረበት ሰው ከሆነ ይፁመው።
64- አንድ ሙስሊም ሴት የአንድ ምሽት መንገድ ከርሷ ጋር የዝምድና ባለቤት የሆነ ወንድ ከሌለ በቀር ልትጓዝ አልተፈቀደላትም።
65- ጾመኛ መሆኑን ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙን ይሙላ። ያበላውና ያጠጣው አላህ ነውና።
71- የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመከራ ወቅት ከምትጮህ፣ ከምትላጭና ልብሷን ከምትቀዳድድ ራሳቸውን አጥርተዋል።
81- የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የሴት ልጅ አለባበስን የሚለብስን ወንድና የወንድ ልጅ አለባበስን የምትለብስ ሴትን ረገሙ።
89- ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም!" "የአላህ መልክተኛ ሆይ ማን ነው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ጎረቤቱ ተንኮሉን ያላመነው ሰው ነው።" አሉ።