إعدادات العرض
ስነ-ምግባራዊ ፊቅህ
ስነ-ምግባራዊ ፊቅህ
1- 'ከትልልቅ ወንጀሎች ትልቁን አልነግራችሁምን?
2- አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።
4- ሲሸጥም፣ ሲገዛም ይሁን ያበደረውን ሲያስመልስ ገር የሆነን ሰው አሏህ ይዘንለት።
5- ሰዎች ጋር የሚበዳደር አንድ ሰውዬ ነበር። ለሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ 'ምናልባት አላህ እኛንም ይቅር ቢለን
6- አላህ በሁሉም ነገሮች ላይ ኢሕሳን (እንድናሳምር) ፅፏል።
7- አትቆጣ!
8- ፍትሃዊዎች (የትንሳኤ ቀን) አላህ ዘንድ በብርሃን በተሰራ ወንበር ላይ ከአርራሕማን ቀኝ በኩል ይሆናሉ። ሁለቱም የአላህ እጆች ቀኝ ናቸው።
9- አደራችሁን ጥርጣሬን ተጠንቀቁ! ጥርጣሬ እጅግ ውሸት የሆነ ወሬ ነውና።
10- ከመልካም ነገር አንዳችም አታሳንስ ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን እንኳ (እንዳታሳንስ)።
11- ብርቱ የሚባለው ታግሎ ያሸነፈ ሳይሆን በቁጣ ወቅት እራሱን የተቆጣጠረ ነው።
12- ወደ መልካም የጠቆመ ሰው የሰሪውን ምንዳ አምሳያ ይመነዳል።
14- በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል!
15- ለሰዎች የማይራራን አሸናፊና የበላይ የሆነው አላህ አይራራለትም።
16- ከሰዎች ሁሉ አላህ ዘንድ እጅግ የተጠላው ደረቅ ተከራካሪ የሆነ ሰው ነው።
19- በእውነተኝነት ላይ አደራችሁን! እውነተኝነት ወደ መልካም ይመራል። መልካም ነገር ደግሞ ወደ ጀነት ይመራልና።
20- ከወንድሙ ክብር የተከላከለ ሰው በትንሳኤ ቀን አላህ እሳትን ከፊቱ ይከላከልለታል።
21- 'ከአማኞች መካከል ኢማናቸው የተሟላው ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ የሆኑት ናቸው ፤ ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ምርጥ የሆኑት ናቸው።'
22- በአንድ ነገር ውስጥ ገራገርነት (ልስላሴ) አይኖርም ያስዋበው ቢሆን እንጂ ፤ ከአንድ ነገር ውስጥ ደግሞ አይነሳም አስቀያሚ የሚያደርገው ቢሆን እንጂ።
23- 'አንድ ሙእሚን በመልካም ስነምግባሩ የፆመኛና (የሌሊት) ሰጋጅን ደረጃ ያገኛል።'
24- ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'
25- 'አላህ በዳይን ያዘገየዋል። የያዘው ጊዜ ግን አይለቀውም!
27- ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።
28- የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፀጉርን አንዱን ተላጭቶ አንዱን ትቶ ከመቆረጥ ከልክለዋል።
29- ዑመር ዘንድ ነበርንና እንዲህ አሉ: 'ከአቅም በላይ ከመጣጣር ተከልክለናል።'
31- አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።
32- በደልን ተጠንቀቁ! በደል የትንሳኤ ቀን ድርብርብ ጨለማዎች ነውና። ስስትንም ተጠንቀቁ! ስስት ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች አጥፍቷልና።
33- ወንድ ልጅ ወደ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ አይመልከት! ሴት ልጅም ወደ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ አትመልከት!
34- ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው። ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።