إعدادات العرض
የአምልኮ ፊቂህ - الصفحة 2
የአምልኮ ፊቂህ - الصفحة 2
1- እርሱ ውሃው አፅጂ ነው፤ ውስጡ የሞተም ሐላል ነው።
2- ውሃው ሁለት 'ቁለተይን' ከደረሰ ነጃሳን አይሸከምም።
3- አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ ሶስት ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ ያውጣ፤ ሸይጧን በአፍንጫው ውስጥ ያድራልና።
7- አንዳችሁ ዉዱእ አድርጎ ኹፎቹን የለበሰ እንደሆነ እነርሱን እንደለበሰ ይስገድ። በነርሱም ላይ ያብስና ከዚያም ለጀናባ ካልሆነ በቀር ከፈለገ አያውልቃቸው።
8- ከፀዳን በኋላ የሚወጣንን ድፍርስና ዳለቻ ቀለም ፈሳሽ እንደ ምንም ነገር አንቆጥረውም ነበር።
9- 'የወር አበባሽ የሚያግድሽ ቀናት ያክል (ሳትሰግጂ ሳትፆሚ) ቆዪ ከዚያም ታጠቢ።'
10- ለአቅመ አዳም በደረሰ ሰው ላይ ሁሉ የጁሙዓ ቀን መታጠብ፣ ጥርሱን ሊፍቅና ካገኘም ሽቶ መቀባቱ ግዴታ ነው።
11- 'ሴት ልጅ ከርሷ ጋር ባሏ ወይም ዘመዷ ከሌሉ በቀር ሁለት ቀን የሚያስኬድ መንገድን አትጓዝ።
14- አንዳችሁ ትከሻዎቹ ላይ አንዳችም ነገር የሌለ ሆኖ በአንድ ልብስ ብቻ አይስገድ።
16- ሱጁድ በወረድክ ጊዜ መዳፎችህን መሬት ላይ አኑር! ክንድህንም ከፍ አድርግ!
19- ከሁሉም ግዴታ ሶላት በኋላ አየተል ኩርሲይን የቀራ ሰው ጀነት ለመግባት ከሞት በቀር ምንም አይከለክለውም።
21- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከዝሁር በፊት አራት ረከዓና ከፈጅር በፊት ሁለት ረከዓ አይተዉም ነበር።
22- ከዝሁር በፊት አራት ረከዓዎች ላይና ከዝሁር በኋላ አራት ረከዓዎች ላይ የተጠባበቀ ሰው አላህ እሳትን በርሱ ላይ እርም አድርጎለታል።
27- እነዚህ ሁለት ሶላቶች በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባድ ሶላት ናቸው። በነዚህ ሶላቶች ያለውን ምንዳ ብታውቁ ኖሮ በጉልበታችሁ እየዳኻችሁም ቢሆን ትመጡ ነበር።
28- ከሶስት ዓይነት አካላት ላይ ብእር ተነስቷል። የተኛ ሰው እስኪነቃ ድረስ፤ ህፃን ልጅ አቅመ አዳም እስኪደርስ ድረስ እና እብድ ጤነኛ እስኪሆን ድረስ ነው።
29- አጋርያንን በገንዘባችሁ፣ በነፍሳችሁና በምላሳችሁ ታገሉ።
31- አላህ አንድ ባሪያ በአንድ ቦታ እንዲሞት የወሰነ ጊዜ ወደዚያ ስፍራ የሚሄድበትን ምክንያት ያደርግለታል።
32- እኔ የበኑ ሰዕድ ቢን በክር ወንድም ዲማም ቢን ሠዕለባህ ነኝ።" አላቸው።
33- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ሶላት ወቅት ዉዱእ ያደርጉ ነበር።
34- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ አንድ ጊዜ ዉዱእ አደርገዋል።
35- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለት ሁለት ጊዜ ዉዱእ አድርገዋል።
37- እያንዳንዱ ሙስሊም በየሰባት ቀኑ አንድ ጊዜ ገላውን መታጠብ አለበት። ሲታጠብም ጭንቅላቱንም ገላውንም መታጠብ አለበት።
38- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ እስልምናን መቀበል ፈልጌ መጣሁ። እሳቸውም በውሃና በቁርቁራ ቅጠል እንድታጠብ አዘዙኝ።
39- አዛን ባዩን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ።
40- ለአላህ ብሎ መስጂድን የገነባ አላህም ለርሱ አምሳያውን ጀነት ውስጥ ይገነባለታል።›' አለ።
41- በዚህ መስጂዴ የሚሰገድ ሶላት ከርሱ ውጪ ከሚሰገዱ አንድ ሺህ ሶላቶች የተሻለ ነው። የተከበረው መስጊድ (መስጂደል ሐራም) ሲቀር።
42- አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ ይስገድ።
44- ‹ቢላል ሆይ! ሶላትን ኢቃም ብለህ በሶላት እረፍት ስጠን።›'
45- እናንተ ሰዎች ሆይ! ይህንን የፈፀምኩት በኔ እንድትከተሉና አሰጋገዴንም እንድታውቁ ነው።'
46- ‹ሶላትን መስገድ የፈለጋችሁ ጊዜ ሰልፋችሁን አስተካክሉ። ከዚያም አንድ ሰው ይምራችሁ። ኢማሙ ተክቢራ ያደረገ ጊዜ እናንተም ተክቢራ አድርጉ!
49- የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሩኩዕ ወገባቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜ "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ
50- 'ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ እንዲህ ይሉ ነበር
52- ይሄ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ስሜት የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ! ወደ ግራህም ሶስት ጊዜ ትፋ!
54- የአላህ መልክተኛ ሆይ! የሰዕድ እናት ሞተች ማንኛው ምፅዋት ነው በላጩ? እርሳቸውም "ውሃ" አሉ። እርሱም ጉድጓድ ቆፈረና "ይህቺ ለሰዕድ እናት ነው።" አለ።
56- ረመዳን የመጣ ጊዜ ዑምራ አድርጊ። በረመዳን የሚደረግ ዑምራ ሐጅ ከማድረግ ጋር ይስተካከላል።" አሏት።
63- ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ነበርኩ። ወደ ቆሻሻ መጣያ ዘንድ ሲደርሱ ቆመው ሸኑ።
65- ጀናዛን ፈጠን ብላችሁ ቅበሩ። ጀናዛው መልካም ከሆነ ወደ መልካም ነገር ማስቀደም ነው። ከዛ ውጪ ከሆነ ደግሞ መጥፎ ነገር ነው ከትከሻችሁ ማላቀቅ ነው።
71- ጀነት ውስጥ ረያን የሚባል በር አለ። የትንሳኤ ቀን ጾመኞች በርሱ በኩል ይገባሉ። በርሱ በኩልም ከነርሱ ውጪ አንድም ሰው አይገባም።
83- በየሁሉም ሁለት አዛኖች መካከል ሶላት አለ። በየሁሉም ሁለት አዛኖች መካከል ሶላት አለ።" ቀጥለው በሶስተኛው "ለፈለገ ሰው" አሉ።
88- እኔ የማትጎዳና የማትጠቅም ድንጋይ መሆንህን አውቃለሁ። እኔ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሲስሙህ ባላይህ ኖሮ አልስምህም ነበር።
89- ተመለስና ደግመህ ስገድ! አንተ አልሰገድክም።
92- አንተ አቡ ሰዒድ ሆይ! በአላህ ጌትነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ ነቢይነት የወደደ ሰው ለርሱ ጀነት ግድ ሆናለታለች።
93- በአላህ መንገድ ላይ አንድ ቀን የጾመ ሰው አላህ ፊቱን ከእሳት ሰባ ዓመታት ያርቀዋል።
94- ሰዎች ማፍጠርን እስካቻኮሉ ድረስ መልካም ላይ ከመሆን አይወገዱም።
98- ሰሑር ተመገቡ! በሰሑር ውስጥ በረከት አለ።
99- ከረመዷን አንድ ቀንም ሆነ ሁለት ቀን በፊት ቀድማቹህ አትፁሙ። ነገር ግን ያስለመደው ጾም የነበረበት ሰው ከሆነ ይፁመው።
