إعدادات العرض
የአምልኮ ፊቂህ
የአምልኮ ፊቂህ
1- ሚስቱን ሳይገናኝ እንዲሁም ሳያምፅ ለአሏህ ሐጅ አድርጎ የተመለሰ ልክ እናቱ እንደወለደችበት ቀን (ከወንጀል ንፁህ) ሆኖ ይመለሳል።
2- ምግብ ቀርቦ አልያም ሁለቱ ቆሻሻዎች እያጨናነቁት ሶላት የለም።
3- የጁሙዐ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ሳለ ለባልደረባህ 'ዝም በል!' ካልከው በርግጥም ውድቅ ንግግርን ተናግረሀል።
5- ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለውን ፂም) አሳጥሩ ሪዛችሁን (የመንጋጭላ ፂማችሁን) ልቀቁ!
6- እኔ እንዳደረጉት አይነት ዉዱእ አድርጎ ከዚያም ነፍሱን ምንም በሃሳብ ሳያደፈርስ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው ያሳለፈው ወንጀሉ ተምሮለታል።' አሉ።'
8- በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባዱ ሶላት የዒሻእ ሶላትና የፈጅር ሶላት ናቸው። በውስጧ ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን ይመጡ ነበር
9- አንዳችሁ ዉዱእ በሌለው ጊዜ ዉዱእ እስኪያደርግ ድረስ አላህ ሶላቱን አይቀበለውም።
10- 'ሲዋክ አፍን የሚያጠራ (የሚያፀዳ)፤ የአሏህንም ውዴታ የሚያስገኝ ነው።'
11- ከባባዶቹን ወንጀሎች ከተጠነቀቁ አምስቱ ሶላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው የተሰሩትን ወንጀሎች ያስሰርዛሉ።
12- (ግዴታነቱን) አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አስቦ የረመዳንን ወር የፆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።
13- መወሰኛይቱን ሌሊት (ለይለቱል ቀድርን) በአላህ አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ኃጢዓቱ ይማርለታል።
14- ሟቾችን አትሳደቡ! እነርሱ ወዳስቀደሙት (ስራቸው) ሂደዋልና።
15- የሱብሒን ሶላት የሰገደ ሰው በአላህ ከለላ ስር ነው።
17- አላህ እንዲህ ብሏል 'የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ላንተም ይሰጥሃል!'
18- የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሁሉም ሶላቶች በኋላ እነዚህን ውዳሴዎች ይሉ ነበር።'
19- 'ከነዚህ ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራዎች ወደ አላህ ተወዳጅ የሚሆኑበት ምንም ቀን የለም።' ማለትም አስሩ የዙልሂጃ ቀናቶች ናቸው።
20- የዐስርን ሶላት የተወ ሰው በርግጥም ስራው ተበላሸ።'
21- ውዱእን አሳምሮ ያደረገ ወንጀሎቹ ከጥፍሮቹ ስር ሳይቀር ከሰውነቱ ባጠቃላይ ይወጣሉ።'
22- 'መቃብሮች ላይ አትቀመጡ! ወደርሷም አትስገዱ!'
23- እነዚህ ከመካከላቸው መልካም (ጻድቅ) ባርያ ወይም መልካም ሰው ሲሞት በመቃብሩ ላይ መስገጃን የሚገነቡ
24- በሰባት አጥንቶቼ ሱጁድ እንዳደርግ ታዝዣለሁ።
26- አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም
27- 'ቁመህ! ካልቻልክ ተቀምጠህ ካልቻልክ በጎንህ ተጋድመህ ስገድ። '
28- የሶላትን ጥሪ ትሰማለህን?' አሉት። እርሱም 'አዎን' አላቸው። እሳቸውም 'እንግዲያውስ ለጥሪው መልስ ስጥ!' አሉት።
29- በቃል ኪዳን ስር ያለን (ሙዓሀድን) የገደለ ሰው የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታዋ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት በኃላ ነው።
31- እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ (ከተቀበልኩ) ከቆጠርኩና
34- 'አዛን ባዩ: 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) ያለ ጊዜ አንዳችሁ ከልቡ 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' ካለ፤
35- ሶላትን የረሳ ሰው ባስታወሰው ጊዜ ይስገድ። ከዚህ በቀር ማካካሻ የለውም።
36- 'በሰውየውና በሺርክ፣ በክህደት መካከል ያለው (ግርዶ) ሶላትን መተው ነው።'
37- 'በኛና በነርሱ (በከሀዲዎች) መካከል ያለው (መለያ) ቃል ኪዳን ሶላት ነው። ሶላትን የተወ ሰው በርግጥም ክዷል።'
39- "የአላህ ቃል የበላይ እንድትሆን አስቦ የተዋጋ ሰው በአላህ መንገድ ተጋደለ የሚባለው እርሱ ነው።" አሉ።
40- (የአዛንን) ጥሪ በሰማችሁ ጊዜ ሙአዚኑ (አዛን አድራጊው) እንደሚለው በሉ።
41- እኔ ንፁህ እንደሆነ ነው ያደረግኳቸውና ተዋቸው።
42- ይህ የደም ስር መቆረጥ ነው። ባይሆን የወር አበባ ስታይበት በነበርሽው የቀናት ልክ ሶላትን ተይ! ከዚያም ታጠቢና ስገጂ።' አሏት።
43- ሰልፋችሁን አስተካክሉ! ሰልፍ ማስተካከል ሶላትን ከሚሞሉት መካከል ነውና።
44- አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው።
45- ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አስር ረከዓዎችን ሸምድጃለሁ።
47- መፀዳጃ ቦታ የመጣችሁ ጊዜ ወደ ቂብላ አትዙሩም ጀርባ አትስጡም! ነገር ግን ወደ ምስራቅ ወይም ምዕራብ ዙሩ
50- የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት በሚከፍቱበት ወቅትና
51- የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጄ በእጃቸው መካከል ሆኖ አንድን የቁርአን ምእራፍ እንደሚያስተምሩኝ ተሸሁድን አስተማሩኝ።
52- አላህ ሆይ! እኔ ከቀብር ቅጣት፣ ከእሳት ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተና እና ከመሲሕ ደጃል ፈተና ባንተው እጠበቃለሁ።' እያሉ ዱዓእ ያደርጉ ነበር።
53- 'አልላሁምመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጧያየ ከማ ባዐድተ በይነል መሽሪቂ ወልመጝሪብ
57- ከጀናባ አስተጣጠብ ሁኔታ
63- የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ አደረጉላቸው።
79- 'ሰውዬው በህብረት የሚሰግደው ሶላት በቤቱ ወይም በሱቁ ከሚሰግደው ሶላት ሀያ ምናምን ደረጃ ትበልጣለች።
81- 'ንገሩኝ እስኪ! አንዳችሁ በር ላይ በየቀኑ አምስት ጊዜ የሚታጠብበት ወንዝ ቢኖር ይህ ከእድፉ ያስቀራል ትላላችሁን?
82- ልጆቻችሁን ሰባት አመት ሲሆኑ በሶላት እዘዟቸው፤ አስር አመት ሲሞላቸው ሶላት ላለመስገዳቸው ምቷቸው፤ በመካከላቸውም የመኝታ ስፍራቸውን ለዩ!
84- የመጽሐፉን መክፈቻ (ፋቲሓን) ያላነበበ ሰው ሶላት የለውም።
104- አንዳችሁ ዉዱእ አድርጎ ኹፎቹን የለበሰ እንደሆነ እነርሱን እንደለበሰ ይስገድ። በነርሱም ላይ ያብስና ከዚያም ለጀናባ ካልሆነ በቀር ከፈለገ አያውልቃቸው።
105- ከፀዳን በኋላ የሚወጣንን ድፍርስና ዳለቻ ቀለም ፈሳሽ እንደ ምንም ነገር አንቆጥረውም ነበር።
106- 'የወር አበባሽ የሚያግድሽ ቀናት ያክል (ሳትሰግጂ ሳትፆሚ) ቆዪ ከዚያም ታጠቢ።'
107- ለአቅመ አዳም በደረሰ ሰው ላይ ሁሉ የጁሙዓ ቀን መታጠብ፣ ጥርሱን ሊፍቅና ካገኘም ሽቶ መቀባቱ ግዴታ ነው።
108- 'ሴት ልጅ ከርሷ ጋር ባሏ ወይም ዘመዷ ከሌሉ በቀር ሁለት ቀን የሚያስኬድ መንገድን አትጓዝ።
116- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከዝሁር በፊት አራት ረከዓና ከፈጅር በፊት ሁለት ረከዓ አይተዉም ነበር።
121- እነዚህ ሁለት ሶላቶች በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባድ ሶላት ናቸው። በነዚህ ሶላቶች ያለውን ምንዳ ብታውቁ ኖሮ በጉልበታችሁ እየዳኻችሁም ቢሆን ትመጡ ነበር።
122- ከሶስት ዓይነት አካላት ላይ ብእር ተነስቷል። የተኛ ሰው እስኪነቃ ድረስ፤ ህፃን ልጅ አቅመ አዳም እስኪደርስ ድረስ እና እብድ ጤነኛ እስኪሆን ድረስ ነው።
125- አላህ አንድ ባሪያ በአንድ ቦታ እንዲሞት የወሰነ ጊዜ ወደዚያ ስፍራ የሚሄድበትን ምክንያት ያደርግለታል።
126- እኔ የበኑ ሰዕድ ቢን በክር ወንድም ዲማም ቢን ሠዕለባህ ነኝ።" አላቸው።
127- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ሶላት ወቅት ዉዱእ ያደርጉ ነበር።
128- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ አንድ ጊዜ ዉዱእ አደርገዋል።
129- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለት ሁለት ጊዜ ዉዱእ አድርገዋል።
131- እያንዳንዱ ሙስሊም በየሰባት ቀኑ አንድ ጊዜ ገላውን መታጠብ አለበት። ሲታጠብም ጭንቅላቱንም ገላውንም መታጠብ አለበት።
132- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ እስልምናን መቀበል ፈልጌ መጣሁ። እሳቸውም በውሃና በቁርቁራ ቅጠል እንድታጠብ አዘዙኝ።
133- ሙአዚኑን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ።
134- ለአላህ ብሎ መስጂድን የገነባ አላህም ለርሱ አምሳያውን ጀነት ውስጥ ይገነባለታል።›' አለ።
135- በዚህ መስጂዴ የሚሰገድ ሶላት ከርሱ ውጪ ከሚሰገዱ አንድ ሺህ ሶላቶች የተሻለ ነው። የተከበረው መስጊድ (መስጂደል ሐራም) ሲቀር።
136- አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ ይስገድ።
138- ‹ቢላል ሆይ! ሶላትን ኢቃም ብለህ በሶላት እረፍት ስጠን።›'
139- እናንተ ሰዎች ሆይ! ይህንን የፈፀምኩት በኔ እንድትከተሉና አሰጋገዴንም እንድታውቁ ነው።'
140- ‹ሶላትን መስገድ የፈለጋችሁ ጊዜ ሰልፋችሁን አስተካክሉ። ከዚያም አንድ ሰው ይምራችሁ። ኢማሙ ተክቢራ ያደረገ ጊዜ እናንተም ተክቢራ አድርጉ!
143- የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሩኩዕ ወገባቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜ "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ
144- 'ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ እንዲህ ይሉ ነበር
146- ይሄ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ስሜት የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ! ወደ ግራህም ሶስት ጊዜ ትፋ!
148- የአላህ መልክተኛ ሆይ! የሰዕድ እናት ሞተች ማንኛው ምፅዋት ነው በላጩ? እርሳቸውም "ውሃ" አሉ። እርሱም ጉድጓድ ቆፈረና "ይህቺ ለሰዕድ እናት ነው።" አለ።
152- ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ነበርኩ። ወደ ቆሻሻ መጣያ ዘንድ ሲደርሱ ቆመው ሸኑ።