إعدادات العرض
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች
3- የሚያጠራጥርህን ነገር ተውና ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ!
4- አላህ ሁሉም ነገር ላይ መልካምነትን ጽፏል፤
5- እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ ከቆጠርኩና (ከተቀበልኩ)
7- ራስን መጉዳትም ሆነ ሌላውን መጉዳት የለም።
10- ግንኙነትና ፆታዊ ስሜትን የሚያነሳሱን ሳይፈፅምና ሳያምፅ ለአሏህ ሐጅ አድርጎ የተመለሰ ልክ እናቱ እንደወለደችው ቀን (ከወንጀል ንፁህ) ሆኖ ይመለሳል።
11- ምግብ ቀርቦ አልያም ሁለቱ ቆሻሻዎች እያጨናነቁት ሶላት የለም።
12- የጁሙዐ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ሳለ ለባልደረባህ 'ዝም በል!' ካልከው በርግጥም ውድቅ ንግግርን ተናግረሀል።
14- ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለውን ፂም) አሳጥሩ ሪዛችሁን (የመንጋጭላ ፂማችሁን) ልቀቁ!
15- እኔ እንዳደረጉት አይነት ዉዱእ አድርጎ ከዚያም ነፍሱን ምንም በሃሳብ ሳያደፈርስ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው ያሳለፈው ወንጀሉ ተምሮለታል።' አሉ።'
16- አሏህ ሆይ! ቀብሬን ጣኦት
17- በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባዱ ሶላት የዒሻእ ሶላትና የፈጅር ሶላት ናቸው። በውስጧ ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን ይመጡ ነበር
18- አንዳችሁ ዉዱእ በሌለው ጊዜ ዉዱእ እስኪያደርግ ድረስ አላህ ሶላቱን አይቀበለውም።
19- 'ሲዋክ አፍን የሚያጠራ (የሚያፀዳ)፤ የአሏህንም ውዴታ የሚያስገኝ ነው።'
20- ትላልቅ ወንጀሎችን ከተጠነቀቀ አምስቱ ሶላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው የተሰሩትን ወንጀሎች ያስሰርዛሉ።
22- (ግዴታነቱን) አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አስቦ የረመዳንን ወር የፆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።
23- መወሰኛይቱን ሌሊት (ለይለቱል ቀድርን) በአላህ አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ኃጢዓቱ ይማርለታል።
24- በተውኳችሁ ላይ ተዉኝ። ከናንተ በፊት የነበሩት ህዝቦች የጠፉት በመጠየቃቸውና ነቢያቶቻቸውን በመቃረናቸው ነው።
25- ሐላል (የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው።
26- አላህ በሁሉም ነገሮች ላይ ኢሕሳን (እንድናሳምር) ፅፏል።
27- አውቆ መጉዳትም ሆነ ሳያውቁ መጎዳዳትም የለም (አይቻልም)። ጎጂን አላህ ይጎዳዋል። ሰዎችን ያስጨነቀ አላህ ያጨናንቀዋል።
28- (ጎረቤቴን) ያስወርሰዋል ብዬ እስከማስብ ድረስ ጂብሪል በጎረቤት (ሐቅ ዙሪያ) እኔን ከማዘዝ አልተወገደም።
29- ማነብነብ (ሩቃ) ፣ ሂርዝ ማንጠልጠልና መስተፋቅር ሽርክ ናቸው።
30- ሟቾችን አትሳደቡ! እነርሱ ወዳስቀደሙት (ስራቸው) ሂደዋልና።
31- የሱብሒን ሶላት የሰገደ ሰው በአላህ ከለላ ስር ነው።
33- 'ከአማኞች መካከል ኢማናቸው የተሟላው ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ የሆኑት ናቸው ፤ ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ምርጥ የሆኑት ናቸው።'
34- ዱንያ መጣቀሚያ ናት። ከዱንያ መጣቀሚያዎች ምርጡ መልካም ሚስት ናት።
35- አላህ እንዲህ ብሏል 'የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ላንተም ይሰጥሃል!'
36- 'ልታሟሉት ከሚገቡ መስፈርቶች ሁሉ ልታሟሉት እጅግ የተገባው ብልትን ሐላል ያደረጋቹበትን መስፈርት ነው።'
37- የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሁሉም ሶላቶች በኋላ እነዚህን ውዳሴዎች ይሉ ነበር።'
38- 'ከነዚህ ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራዎች ወደ አላህ ተወዳጅ የሚሆኑበት ምንም ቀን የለም።' ማለትም አስሩ የዙልሂጃ ቀናቶች ናቸው።
39- የዐስርን ሶላት የተወ ሰው በርግጥም ስራው ተበላሸ።'
40- ውዱእን አሳምሮ ያደረገ ወንጀሎቹ ከጥፍሮቹ ስር ሳይቀር ከሰውነቱ ባጠቃላይ ይወጣሉ።'
41- ሰውዬው (ምንዳ እንደሚያገኝበት) እያሰበ ለቤተሰቡ ወጪ ያወጣ ጊዜ ለርሱ ምፅዋት ትሆንለታለች።
42- የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፀጉርን አንዱን ተላጭቶ አንዱን ትቶ ከመቆረጥ ከልክለዋል።
43- 'መቃብሮች ላይ አትቀመጡ! ወደርሷም አትስገዱ!'
44- እነዚህ ከመካከላቸው መልካም (ጻድቅ) ባርያ ወይም መልካም ሰው ሲሞት በመቃብሩ ላይ መስገጃን የሚገነቡና
45- በሰባት አጥንቶቼ ሱጁድ እንዳደርግ ታዝዣለሁ።
47- አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም
48- 'ቁመህ ስገድ! ካልቻልክ ተቀምጠህ ስገድ! ካልቻልክ በጎንህ ተጋድመህ ስገድ። '
49- የሶላትን ጥሪ ትሰማለህን?' አሉት። እርሱም 'አዎን' አላቸው። እሳቸውም 'እንግዲያውስ ለጥሪው መልስ ስጥ!' አሉት።
50- የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ የጉዳይ ጊዜ ኹጥባን (ኹጥበቱል ሓጃህ) አስተማሩን
52- በቃል ኪዳን ስር ያለን (ሙዓሀድን) የገደለ ሰው የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታዋ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት በኋላ ነው።
53- የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በፍርድ አሰጣጥ ዙሪያ ጉቦ ሰጪንም ተቀባይንም ረገሙ።
55- እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ (ከተቀበልኩ) ከቆጠርኩና
57- ተረከዞቻቸውን የዉዱእ ውሃ የማያስነኩ ከእሳት ወዮላቸው! ዉዱእን አዳርሳችሁ አድርጉ!
58- 'አዛን ባዩ: 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) ያለ ጊዜ አንዳችሁ ከልቡ 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' ካለ፤
59- ሶላትን የረሳ ሰው ባስታወሰው ጊዜ ይስገድ። ከዚህ በቀር ማካካሻ የለውም።
60- 'በሰውየውና በሺርክ፣ በክህደት መካከል ያለው (ግርዶ) ሶላትን መተው ነው።'
61- 'በኛና በነርሱ (በከሀዲዎች) መካከል ያለው (መለያ) ቃል ኪዳን ሶላት ነው። ሶላትን የተወ ሰው በርግጥም ክዷል።'
63- ከስለት ከለከሉ። እንዲህም አሉ "እርሱ መልካምን ይዞ አይመጣም። በስለት የሚገኘው ትርፍ ስስታም ተገዶ ማውጣቱ ብቻ ነው።
65- የትንሳኤ ቀን በሰዎች መካከል መጀመሪያ የሚፈረደው ጉዳይ የደም ጉዳይ ነው።
66- የአላህ ቃል የበላይ እንድትሆን አስቦ የተዋጋ ሰው በአላህ መንገድ ተጋደለ የሚባለው እርሱ ነው።" አሉ።
67- (የአዛንን) ጥሪ በሰማችሁ ጊዜ ሙአዚኑ (አዛን አድራጊው) እንደሚለው በሉ።
68- እኔ ንፁህ እንደሆነ ነው ያደረግኳቸውና ተዋቸው።
69- ይህ የደም ስር መቆረጥ ነው። ባይሆን የወር አበባ ስታይበት በነበርሽው የቀናት ልክ ሶላትን ተይ! ከዚያም ታጠቢና ስገጂ።' አሏት።
70- ሰልፋችሁን አስተካክሉ! ሰልፍ ማስተካከል ሶላትን ከሚሞሉት መካከል ነውና።
71- አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው።
72- ዱንያ ጣፋጭና አረንጓዴ (ለምለም) ናት። አላህም እንዴት እንደምትሰሩ ሊያያችሁ በውስጧ ምትኮች አድርጓችኋል። ዱንያንም ተጠንቀቁ! ሴቶችንም ተጠንቀቁ!
73- ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አስር ረከዓዎችን ሸምድጃለሁ።
74- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሌሊት የተነሱ ጊዜ አፋቸውን በመፋቂያ ይፍቁ ነበር።
75- አንድ አማኝ ወንድ አንዲትን አማኝ እንስት አይጥላ። ከርሷ አንድ ባህሪዋን ቢጠላ እንኳ ሌላ የሚወደው ባህሪ አላትና።
76- መፀዳጃ ቦታ የመጣችሁ ጊዜ ወደ ቂብላ አትዙሩም ጀርባ አትስጡም! ነገር ግን ወደ ምስራቅ ወይም ምዕራብ ዙሩ
77- አንዳችሁ እየሸና ሳለ ብልቱን በቀኝ እጁ አይያዘው፤ ሲፀዳዳም በቀኝ እጁ አይጥረግ፤ በእቃ ውስጥም አይተንፍስ!
79- የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት በሚከፍቱበት ወቅትና
80- የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጄ በእጃቸው መካከል ሆኖ አንድን የቁርአን ምእራፍ እንደሚያስተምሩኝ ተሸሁድን አስተማሩኝ።
81- አላህ ሆይ! እኔ ከቀብር ቅጣት፣ ከእሳት ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተና እና ከመሲሕ ደጃል ፈተና ባንተው እጠበቃለሁ።'
82- 'አልላሁምመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጧያየ ከማ ባዐድተ በይነል መሽሪቂ ወልመግሪብ
83- ውሻ ከአንዳችሁ እቃ የጠጣ ጊዜ (እቃውን) ሰባት ጊዜ ይጠበው።
85- የእውነት ሰማእትነትን እንዲሰጠው አላህን የጠየቀ ሰው ፍራሹ ላይ ቢሞት እንኳ አላህ የሰማእታትን ደረጃ ያደርሰዋል።
86- ከጀናባ አስተጣጠብ ሁኔታ
91- በአላህ እምላለሁ! ለአንተ ቀይ ግመል ከሚኖርህ በአንተ ሰበብ አላህ አንድ ሰው ቢመራልህ የተሻለ ነው።
92- በአላህ መንገድ የሚዘምትን ያሰናዳ ሰው በርግጥም ዘምቷል። በአላህ መንገድ ለዘመተ ሰው (ቤተሰብ) በመልካም ትብብሩ የተተካ በርግጥም ዘምቷል።
93- የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ አደረጉላቸው።
98- አላህ እንዲህ ብሏል: ‹ሁሉም የአደም ልጅ ስራ ለርሱ ነው ፆም ሲቀር፤ ፆም ለኔ ነው። በርሱ የምመነዳውም እኔው ነኝ።
